ሃሰተኛ ዘገባዎችን በማሰራጨት የተጠመዱ ግለሰቦችን ማጋለጥ እንደሚገባ የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

በማህበራዊ የትስስር ገጾች በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ ፣ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት የሚሯሯጡ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ሊቆጠብ እንደሚገባው ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ከሰሞኑ በማህራዊ የትስስር ገፅ ላይ አንድን የፌደራል ፓሊስ አባል ምስል ባልተገባ መልኩ አቀናብሮ በመጠቀም እና ይህን የተሳሳተ ምስልም ባልተገባ መልኩ የሰዎችን ትኩረት እንዲሰብ እንዲሁ በዋናነት ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ጥረት እንደተደረገ ተመልክተናል ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን ለኢትዮ ኤፍኤም የገለፁት የፌደራል ፓሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ጄላን ኡመርን ይህ ድርጊት ፈፅሞ ተገቢ እንዳይደለ ገልፀውልናል፡፡

በተዛባና የተንኮል ኢላማ ባነገበ መልኩ የፌደራል ፓሊስ ኮምሽኑ አባላትን የደንብ ልብስ እና ምስል ባልተገባ መልኩ በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚሯሯጡ አካላትም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኮምሽኑ አሳስቧል፡፡

እንዲህ መሰሉን ትክክል ያልሆነ ተግባርም ህብረተሰቡ ማጋለጥ እንደሚገባው ነግረውናል፡፡ Ethio FM