ትኩረት በአፍሪካ

የቻድ የምርጫ ኮሚሽን ባለፈው እሁድ የተካሔደውን ምርጫ ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። በምርጫው ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቤ እንደሚያሸንፉ የብዙዎች እምነት ነው። በምርጫው ያልተሳተፉት ሳሌሕ ኬብዛቦ የተባሉ ፖለቲከኛ ዴቤ ካሸነፉ ቻድን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አደርጋታለሁ ሲሉ ዝተዋል…