በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈፀመ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ መኮንን ለቢቢሲ ገለጹ። የታጠቀው ኃይል “ቤቶችን ያቃጥላል፤ ሰዎችን ይገድላል” በማለትም ወደ አካባቢው የገባው የፌደራል የጸጥታ መዋቅርና የመከላከያ ሰራዊትም “ከአቅሙ በላይ” መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል።…