በፍጹም ወታደራዊ አማራጭ ቦታ የለዉም፤ የህዳሴዉ ግድብን በተመለከተ መፍትሄ ሊሆንም አይችልም- የሱዳን የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር

Sudan rules out armed action over Ethiopia’s GERD

Sudanese Foreign Minister Mariam al-Sadiq al-Mahdi ruled out military action to stop Ethiopia filling its controversial Blue Nile mega dam, during a visit to Qatar Thursday

የህዳሴዉ ግድብን በተመለከተ ወታደራዊ አማራጭ ቦታ የለዉም በህዳሴዉ ግድብ ላይ ያሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት በሚደረጉ ፖለቲካዊ ዉይይቶች መሆኑን ሱዳን እንደምታምን የሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ተናግረዋል፡፡ሚንስትሯ መርያም አል-ሳድቅ አል-ማህዲ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት በፖለቲካዊ ጉዳዮች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

There is no room to talk about the military option. We are now talking about political options,’ Sudanese Foreign Minister Mariam al-Sadiq al-Mahdi told reporters in Doha

Mariam Al-Sadiq Al-Mahdiከዚህ ዉጭ ግን ወታደራዊ አማራጭ ምንም ቦታ እንደሌለዉ ተናግረዋል፡፡ሚንስትሯ በኳታር ዶሃ ጉብኝት እያደረጉ በነበሩበት ወቅት፣ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ግብጽና ሱዳን ጥቅማችንን ይጎዳል የሚል ስጋት እንዳለባቸዉ ያነሳሉ፤ ወታደራዊ አማራጮች ሊኖሩ ይችላሉ ወይ? በሚል ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ሚንስትሯ ሲመልሱ፣ በፍጹም ወታደራዊ አማራጭ ቦታ የለዉም፤ መፍትሄ ሊሆንም አይችልም ብለዋል፡፡

ከዚህ ይልቅ የዓለም አቀፋ ማህበረሰብ በተለይም ደግሞ የአፍሪካ ሀገራት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ለመፍትሄዉ እንዲተጉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል ሚንስትሯ፡፡ቀደም ሲል የሱዳን የዉሃና መስኖ ሚንስቴር ሱዳን ጉዳዩን እስከ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታዉ ምክር ቤት ድረስ ልትወስደዉ እንደምትችል ተናግረዉ እንደነበር ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

“There is no room to talk about the military option. We are now talking about political options,” al-Mahdi told reporters in Doha.The Grand Ethiopian Renaissance Dam has been a source of tension in the Nile River basin ever since Addis Ababa broke ground on it in 2011.The comments come a day after Ethiopia said it would press on with filling the GERD dam, sparking warnings from Sudan and Egypt.”There will be a significant mobilisation of global opinion — and most importantly African opinion, especially in the neighbouring countries and Nile Basin countries — to prevent Ethiopia from moving ahead with de-stabilizing the security of its significant neighbours, Egypt and Sudan,” she added.

ይሁንና የሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚነስትር አሁን ላይ ጉዳዩን ጎረቤቶቻችን የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት እንዲሰጡት እናደርጋለን ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ፍትሃዊ የሆነ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ዉይይቶችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ስትገልጽ ቆይታለች፡፡አሁንም በዚህ አቋሟ እንደጸናች ናት፡፡የሁለተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌትንም ለማከናወን ምንም የሚያግዳት ሃይል እንደሌለ መግለጿም የሚታወስ ነዉ፡፡

Mariam Al-Sadiq Al-Mahdi