ዳዳብና እና ካኩማ የስደተኛ ካምፖች ሊዘጉ ነው

ኬኒያ በብዙ መቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የአጎራባች ሶማሊያ ስደተኞች የተጠለሉባቸውን ግዙፎቹ ዳዳብ እና ካኩማ የስደተኛ ካምፖች እንዲዘጉ በዛሬው ዕለት ትዕዛዝ ሰጠች። ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዕቅዱን እንዲያቀርብ የሁለት ሳምንት ጊዜ ተሰጥቶታል ሲል የሀገር ደህንነት ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በሰሜን ኬንያ የሚገኙት ዳዳብና ካኩማ የስደተኛ ካምፖች ከ410 ሺህ በላይ ስደተኞች አስጠል…