በህግ ማስከበር ዘመቻው ሁሉንም ሥራ በጥሩ መልኩ ከሰራን በኋላ በር አልሰራንለትም፤ ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ አዳነ
በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ በጥቂት መስዋዕትነት ከተደመደመ በኋላ ዝም ነው የተባለው፣ የትህነግ ኃይሎችና ፖለቲከኞች እንዲሁም ዲያስፖራዎች ዝምታውን ተጠቀሙበት፣
ማይካድራ ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ በከፍተኛ ደረጃ ዶክመንተሪ እየተሰራ የተደረገውን ሁሉ በዝርዝር ለማሳየት ብንሞክር ኖሮ ይህ ሁሉ ባልሆነ ነበር፣
የፖለቲካ ስሪቱ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ አልነበረም፤ይልቁንም ከውጭ የተቀዳና እንዲሁ ረብ በሌለውና ዋልታ ረገጥ በሆኑ ቃላት እርስበርስ የምንባላበት ሁኔታ ነው የነበረው፣
የትህነግ ፕሮግራም ደግሞ ይህችን አገር በቋንቋና በዘር መከፋፈል ነበር፣
ክልል የሚል አደገኛ አጥር ውስጥ ከተውን ‹‹የእኔ ነው፤ የአንቺ ነው›› እየተባባልን 27 ዓመት ሙሉ ስንባላ ኖርን፣ ለ30 ዓመታት መሰረት የጣለ አመለካከት በአንድ ጊዜ ይቀየር ማለት አይቻልም፣
በህወሓት ዘመን ግድያ፣ እስር፣ ጥፍር መንቀል ነበር፤ አሁን ግን ከምንም ነገር የሌለበት ፖለቲካ የማያውቅ ሰርቶ የሚበላ ነው በማይታወቅ አካል እየተገደለ ያለው፣
አሁን ወደኋላ ሄደን የዘር ፖለቲካ የምናራምድበት ጊዜ አልነበረም፣ ፖለቲከኞቻችን እርስበርስ ካባሉን በኋላ አስተካክለው መምራት ባለመቻላቸው ምክንያት ነው ይሄ ለውጥ የመጣው፣
በትክክለኛ ምርጫ ሥልጣኔን አሳልፌ ለመስጠት ፍቃደኛ ነኝ የሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ነው ያለው፤ በእርግጥ ያስረክቡ፤ አያስረክቡ ሌላ ነገር ነው፤ ቢያንስ ግን ይህን የሚል አመራር መኖሩ በራሱ እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀም ይገባል፣
በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች ሊከተሉት የሚገባው የሥነ ምግባር ደምብ አለ፤ ማንኛውም ፓርቲ መተግበር አለበት፣ ‹‹ፕሮግራሜ ለህብረተሰቡ ይጠቅማል›› በሚለው መንገድ ሃሳቡን ለሕዝቡ ሲያደርስ መንግስት ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባል፣
ሱዳን የምታወጣውን መግለጫ ስታይ ያስደነግጥሻል፣ ሱዳን ኢትዮጵያ ወረራ አካሄደችብኝ ነው የምትለው እንጂ እኔ ወርሬያለሁ ብላ አታውቅም፣ ዓላማው መሬት መያዝ ሳይሆን የግድቡን ግንባታ ማጨናገፍ እንደሆነ ህብረተሰቡም ቢሆን ይረዳል ፣
በሱዳን የስደተኞች ጣቢያ ላይ ለምን ወጣቶች ብቻ ተቀመጡ፤ ከዚህ ወንጀል ሰርተው የተደበቁ ስለመሆናቸው በግልፅ ለዓለምአቀፍ ህብረተሰብ ማስረዳት መቻል ነበረብን፣ ትህነግ የፈፀመውን ግፍ የዓለም ሕዝብ እንዲያውቀው አላደረገንም፣
አሁን እየተደረጉ ያሉ ሰላማዊ ሰልፎች ቢጠናከሩና በተከታታይነት ቢቀጥሉ የዓለም አቀፍ ህብረተሰብ እውነቱን እያወቀ ይሄዳል፣
የትህነግን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ህብረተሰብ ባሳወቅን ቁጥር የኢትዮጵያን ሁኔታ በሚዛኑ መታየት ይጀምራል፤ የተጀመረው ነገር መቆም የለበትም፤ በመንግስትም ሊደገፍ ይገባል፣
ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ አዳነ በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በማስመልክት ያነሷቸውን ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=43766