ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሰራጨት ሀገራቸውን ሲሰርቁ የነበሩ 42 ድርጅቶች ዝርዝር

[addtoany]
May be an image of text that says 'የገቢዎ ች ሚኒስቴር ሚኒስቴር & E in A L0 希 Ministry Ministry of Revenues Revenues'የገቢዎች ሚኒስቴር ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሰራጨት ሀገራቸውን ሲሰርቁ የነበሩ 42 ድርጅቶችን ዝርዝር ይፋ አደረገ
በ2013 በጀት ዓመት ባለፉት 7 ወራት 42 ድርጅቶች ሀሰተኛ ደረሰኝ ሲያሰራጩ በጥናት መለየታቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሰራጨት ከተለዩት መካከል በቁጥጥር ስር የዋሉም እንዳሉ ተገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ከተዘረዘሩት ህገ ወጥ ድርጅቶች ግብይት የፈፀሙ አካላት ኦዲት እንደሚደረጉ እና ከዚህ በኋላም ህብረተሰቡ ከድርጅቶቹ ግብይት እንዳይፈፅሙ አሳስቧል።
አንዳንድ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ነግደው ካተረፉት ትርፍ ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን ግብር በታማኝነት መክፈል ሲገባቸው በሀሰተኛ ማንነት እንዲሁም በህይወት በሌለ ሰው ስም ጭምር የንግድ ፍቃድ አውጥተው ህገ ወጥ ንግድ ላይ በመሰማራት ሀገር ማግኘት የሚገባትን ገቢ በማሳጣት የትውልድን ተስፋ እንደሚያጨልሙም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።
ገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም 217 ድርጅቶች በሀሰተኛ ደረሰኝ ከሀገራቸው ሲሰርቁ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አስታውቋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር
No photo description available.
No photo description available.
No photo description available.
No photo description available.
No photo description available.