አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴነት ታገዱ ።

የብአዲን ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት ሁለት ቀናት ሲያደርገው የነበረውን መደበኛ ስብሰባ አጠናቀቀ።

ማዕከላዊ ኮሚቴው በቆይታው የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከነዚህም ውስጥ የድርጅቱ ነባር ታጋይ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በጥረት ኮርፖሬት ላይ በፈጠሩት ችግር ምክንያት በመጪው መስከረም እስከሚካሄዳው የድርጅቱ ጉባኤ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳልፏል።

ኮሚቴው በሀገሪቱ በተጀመረው ለውጥ ዙሪያ ዝርዝር ግምገማ ማካሄዱንና የተጀመረውን ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ መስተላለፉንም ከድርጅቱ ፅህፈት ቤት የገኘነው መረጃ ያመለክታል።