የምስራቅ ጎጃም ዞን አመራሮች ከሕዝብ ጋር ተፋጥጠዋል

የምስራቅ ጎጃም ዞን አመራሮች ከሕዝብ ጋር ተፋጥጠዋል

ሕዝብ በተለያዩ መድረኮች ይነሱልን ያላቸውን አመራሮች እንዲነሱ ቢወሰንም፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን አመራሮች ዛሬ በመርጦለማርያም ስብሰባ አድርገው በሚነሱት ምትክ ለማስቀመጥ ሲጥሩ፣ ሕዝብ “መሪዎቹን መምረጥ ያለበት ሕዝብ ነው” በሚል ከዞኑ አመራሮች ጋር መፋጠጡ ተጠቁሟል።

በተለያዩ መድረኮች በተነሱ ቅሬታዎች መሰረት መሪዎቹን ራሱ መምረጥ እንዳለበት መግለፁንና የዞኑ አመራሮች በድብቅ የወረዳ አመራሮችን ለመምረጥ ጥረት ማድረጋቸው ሕዝብ “አሁንም የሕዝብን ጥቅም የማያስጠብቁትን ሊመርጡብን ነው” የሚል ስጋት እንዳለበት ተግፆአል።