ኢትዮጵያ ወገንተኛ የሆነ ጣልቃ ገብነትን እና በሀገር እና መንግስት ላይ የሚካሄድ ስም የማጥፋት ዘመቻ አትቀበልም

ኢትዮጵያ ወገንተኛ የሆነ ጣልቃ ገብነትን እና በሀገር እና መንግስት ላይ የሚካሄድ ስም የማጥፋት ዘመቻ አትቀበልም-ጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት

ኢትዮጵያ ወገንተኛ የሆነ ጣልቃ ገብነትን እና በሀገር እና መንግስት ላይ የሚካሄድን ፓለቲካዊ ወገንተኝነት ያለውን ስም የማጥፋት ዘመቻ እንደማትቀበል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃውን ተከትሎ እየቀረቡ ስላሉ የሰብዓዊ ድጋፎች እና ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

መግለጫው መንግስት የትግራይ ክልል መልሶ ለመገንባት የሚያርገውን ጥረት የሚያግዙ ዓለም አቀፍ ተባባሪ አካላትን እንደሚያበረታታ ገልጿል።

የዓለም አቀፍ ተባባሪ አካላት ተሳትፎ የሚያስፈልገው የትግራይ ህዝብ ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ መሆኑን ነው ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።

ህግን የማስከበር እርምጃውን ዝቅ ለማድረግ የሚካሄድን አሉታዊ ዘመቻ ኢትዮጵያ እንደማትቀበልም አስታውቋል።

አሁንም መንግስት የወንጀለኛው ቡድን አባላትን እና ጥፋተኞችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ ስራውን እንደሚቀጥል አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ሁሉም ጫፍ ያሉ ዜጎች ባለፉት ሶስት አስርት አመታት በወንጀለኛው የህወሓት ቡድን ምክንያት መስዋዕትነት ከፍለዋል ነው ያለው መግለጫው ።

በአሁን ወቅት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት መስዋዕትነት ሲከፍሉ የቆዩት ኢትዮጵያውያኑ ወደ ዴሞክራሲ ፣ልማት እና ሰላም የሚያርጉትን ጉዞ ጀምረዋል ነው ያለው ፅህፈት ቤቱ።

የፌዴራል መንግስት እነዚህ ዓላማዎችን የሚደግፉ አካላትን እንደሚያስተናግድ አስታውቋል።