ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልፁ።

“በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን”- ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ

በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡

ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀው እስከ አሁን ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አገራችን በልማት፣ በዴሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር መስራቷን እንደምትቀጠል ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሸባሪነትን በመዋጋት እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ እረገድ የአሜሪካ ጠንካራ አጋር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ወደፊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አገራችን በጋራ ትሰራለች ብለዋል ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር