ስርዓት አልበኝነትን ተከትሎ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ በደቡብ ክልል እየተስፋፋ ነው፡፡

በደቡብ ክልል የመሬት ወረራ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑ ተገለፀ
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ምክንያት በማድረግ የመሬት ወረራ እየተስፋፋ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር መነሻ በማድረግ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ በሚያካሄዱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብሏል ፖሊስ፡፡

ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል እንደገለጹት ከሆነ በሀዋሳ ከተማና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች የመሬት ወረራና ህገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሳተፉ አካላትን በመለየት ህግ የማስከበር ተግባር ተጀምሯል፡፡

እንደ ኮሚሽነረየ ገለጻ በክልሉ ስርዓት አልበኝነት እንዳይስፋፋ መላው ህብረተሰብና የጸጥታ አካላት ተቀናጅተው እየሰሩ ነው፡፡

በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩ ቦታዎችን በመለየት ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ