ኢትዮጵያ እንቁላል ከዩክሬን ልታስገባ መሆኑ ተነገረ።

ኢትዮጵያ እንቁላል ከዩክሬን ልታስገባ መሆኑ ተነገረ።

Imageዩክሬን ከፍተኛ የሆነ የእንቁላል ምርትን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረሷን አስታዉቃለች፡፡

ኢትዮጵያ እና ዩክሬን በእንቁላሎቹ ጥራት ዙሪያና ወደ ኢትዮጵያ በሚልኩበት አግባብ ዙሪያ ተወያይተዉ መስማማታቸዉን ዩኬ አር ኢንፎረም የተሰኘ የአገሪቱ ሚዲያ በድረገጹ አስነብቧል፡፡

ስምምነቱ በዘርፉ የተሰማሩ የዩክሬን ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ የገበያ መዳረሻ እንዲያገኙም ያስችላል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ጥራት ያላቸዉ ዕንቁላሎችን ከዩከሬን በማስገባት ለምግብ ፍጆታ እንደምታዉልም ታዉቋል፡፡

ዩክሬን ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በሌሎች አፍሪካ አገራትም የእንቁላል ምርት በገፍ እንድምትልክ አስታዉቃለች፡፡

በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ፤ ጋና፤ ሞሮኮ፤ አልጄሪያ፤ አንጎላና ደቡብ አፍሪካ እንቁላል እንደምታስገባ ተሰምቷል፡፡