ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ሚዲያው ገፃቸው ዛሬ ጠዋት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተናል። በሰብአዊ ርዳታ፣ በጸጥታ ጉዳዮች፣ በመሠረተ ልማት እና በመንግሥት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ያሉ ክንውኖች ተገምግመዋል። በውጤታማነት የተከናወኑ ሥራዎችንና ያጋጠሙ ፈታኝ ሁኔታዎችን በጥልቀት ፈትሸናል። ከአስተዳደሩ ጋር ባካሄድነው ምዘና አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን የለየን ሲሆን፣ አስፈላጊዎቹ ተግባራት እንዲከወኑ አቅጣጫን አስቀምጠናል።ብለዋል።