ጾታዊ ጥቃት የፈጸመ ‘የህግን የመጨረሻ ጥግ ውሳኔ ማግኘት አለበት’ የሚል አቋም ነው ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ያላት- አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ይዞታ፣ በኢትዮጵያ ላይ የሚቀርቡ ውንጀላዎች እና የኢትዮጵያ ምላሽ

“ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ – ይህን የፈጸመ ‘የህግን የመጨረሻ ጥግ ውሳኔ ማግኘት አለበት’ የሚል አቋም ነው ያላት። በዚህላይ ትዕግስት የለም። ትዕግስት ካለም የትዕግስት ደረጃው ዜሮ እና ዜሮ ብቻ ነው” – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ።

VOA – በተባበሩት መንግሥታት ከኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ነው።

በትግራይ ባለው የሰብዓዊ ይዞታ ዙሪያ በመንግሥታቱ ድርጅት ልዩ ልዩ ጽ/ቤቶች እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች የወጡ ዘገባዎችና መግለጫዎች መነሻ በማድረግ አሉላ ከአምባሳደር ታዬ ጋር ካደረገደው ሰፊ ቃለ ምልልስ የመጀመሪያውን ክፍል ይዞ ቀርቧል።