አርቲስት መስከረም ወንድማገኝ አረፈች

አሳዛኝ ዜና – አርቲስት መስከረም ወንድማገኝ አረፈች

ሥርዓተ ቀብሯ ነገ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2010ዓ.ም. በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በ8፡00 ሰዓት ይፈፀማል

ቤተሰቦቿ – መገናኛ 24 ቀበሌ፣ የነገው ሰው ትምህርት ቤት ፈለ ፊት በሚገኘው ማኅበር ቤት የሀዘን ዳስ ተጥሏል፡፡

የ28 ዓመቷ መስከረም …

• ከ10 በላይ ፊልሞች ላይ ተሳትፋለች

• ምንሼ ፊልም ላይ መሪ ገፀ ባህርይ ተጫውታለች

• አልተኛም እና በቅርብ የሚወጣው ላመስግንሽ ፊልም ላይ ተውናለች

• የዳይሬክተር መሐመድ ዳውድ ‹‹ያነገስከኝ›› ፊልም ላይም ፕሮዳክሽን ማናጀር ነበረች

• የሰው ለሰው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ – ተዋናይ፣ ፕሮዳክሽን ማናጀር እና ኮንቲኒቲን መርታለች

• የተቀበረው – ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እንዲሁም የደራሲና መምህር ሀይሉ ፀጋዬ ‹‹የደወል ድምጾች›› የሬዲዮ ድራማ ላይ ተጫውታለች

መስከረም – ለተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ቀረጻ ደብረሲና ከተማ ነበረች፡፡ አመመኝ ብላ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች፡፡

በተለያዩ ሆስፒታሎች ለስድስት ቀናት አልጋ ይዛ ሕክምናዋን እየተከታተለች ነበር፡፡

ይሁንና ዛሬ ጠዋት ሆስፒታል እያለች አርፋለች፡፡

ሥርዓተ ቀብሯ ነገ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2010ዓ.ም. በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በ8፡00 ሰዓት ይፈፀማል

ነፍስ ይማር!