የብላክ ፓንተር -ዋካንዳ የቴክኖሎጂ ከተማ ጭስ አባይ ላይ እውን ትሆናለች፡

በአማራ ክልል የቴክኖሎጂ ከተማ ሊገነባ ነው፡፡

•‹‹የብላክ ፓንተር -ዋካንዳ የቴክኖሎጂ ከተማ ጭስ አባይ ላይ እውን ትሆናለች፡፡›› ዋና ስራ አስፈጻሚው ሚካኤል ካሚል

በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር -ጭስ አባይ ከተማ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ከተማ ሊገነባ ነው፡፡

የቴክኖሎጂ ከተማው በሀብ ሲቲ ላይቭ ኢትዮጵያ በተሰኘ ፕሮጀክት ነው የሚገነባው፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ቦታውን ከወዲሁ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ዛሬ በተካሄደው የመርሃ ግብር ትውውቅ እንዳሉት የቴክኖሎጂ ከተማው የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ልህቀት ያፋጥናል፡፡የቴክኖሎጂ ሽግግሩንም ወደፊት ያስጉዛል ብለዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚካኤል ካሚል ኢትዮጵያ ቀደምት የቴክኖሎጂ ሀገር እና ለቴክኖሎጂ ቅርበት ባለው አባይ ላይ መገኘቷ የቴክኖሎጂ ከተማዋን ለመገንባት ያነሳሳን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱንም በ7 ዓመታት ውስጥ እውን እናደርገዋለን፡፡በብላክ ፓንተር ፊልም ያለችውን የ‹‹ዋካንዳ›› ከተማን በባሕር ዳር እውን እናደርገታለን ብለዋል፡፡

ሰጠኝ እንግዳው አማራ ማስ ሚዲያ ከአዲስ አበባ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE