የደሕንነት ተቋሙ የማሕበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶችን ማስጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ውስጡን ሊያጠራ ይገባል።
–
የማሕበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች የተሳሳቱ መረጃዎች ምንጫቸው የደሕንነት አባላት እንደሆኑ እየሰማን ቢሆንም ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የማሕበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶችን የሚያስጠነቅቅ መግለጫ ማውጣቱን አንብበናል።
–
የደሕንነት ተቋሙ ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡
–
የደሕንነት ተቋሙ መግለጫ መልካምነቱ እንደተጠበቀ ቢሆንም በተቋሙ ውስጥ ያሉ አሰራሮችን ማስተካከል፣ መረጃ የሚበትኑትን ማጥራትና የተዝረከረኩ ስራዎችን ማጥራት ይገባዋል። እንዲሁም በሃገርና ሕዝብ ሰላምና ደሕንነት ላይ የሚያሴሩትን የመንግስት መዋቅር ውስጥ የተወሸቁ ኔትወርኮችን ማስወገድ ከተቋሙ የሚጠበቅ ሐገራዊ ድርሻ ነው። ተቋሙ በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን ችግሮች እያጠራ መሔድ ይገባዋል።