በኢፈርትና በሕወሓት የንግድ ተቋማት የተከማቸው ገንዘብ የትግራይ ሕዝብ ከሰብዓዊ ቀውስ ለማዳን በአስቸኳይ ስራ ላይ ሊውል ይገባል።

በኢፈርትና በሕወሓት የንግድ ተቋማት የተከማቸው ገንዘብ የትግራይ ሕዝብ ከሰብዓዊ ቀውስ ለማዳን በአስቸኳይ ስራ ላይ ሊውል ይገባል። የሕወሓት ቅሪቶች በየስርቻው ተወትፈው የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ ሳናዳምጥ ለንፁሃን ልንደርስላቸው ይገባል።ካሁን በኋላ የቤት ሥራችን የትግራይን ህዝብን መታደግ ነው። የትግራይ ህዝብ በማንነቱ አንገቱን እንዳይደፋና ወገን እንዳለው በተግባር ማሳየት አለብን። ከሰብአዊ እርዳታ እንጀምር። ህዝብና ፖለቲካ መቼም አንድ ሆነው አያውቁም።

Minilik Salsawi – በኢፈርትና በሕወሓት የንግድ ተቋማት የተከማቸው ገንዘብ የትግራይ ሕዝብ ከሰብዓዊ ቀውስ ለማዳን በአስቸኳይ ስራ ላይ ሊውል ይገባል። የሕወሓት ቅሪቶች በየስርቻው ተወትፈው የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ ሳናዳምጥ ለንፁሃን ልንደርስላቸው ይገባል።
የነጮቹ መንግስታትና የእርዳታ ድርጅቶች መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት እያጣጣሉና በትግራይ የተከሰተውን ችግር ሰበብ አድርገው አሻጥራቸውን ተፈጻሚ ለማድረግ በረሐብ ሽፋን ሌላ የጦርነት ነጋሪን ለመጎሰም ያሰፈሰፉ ስለሆነ በፍጥነት ፕሮፓጋንዳቸውን መስበር ያስፈልጋል። ነጮቹ በእርዳታ ሽፋን ትግራይን የጦርነት ሜዳ ለማድረግ ያሰቡትን ሐሳብ ልንሰብረው ይገባል።
የሕወሓት ቅሪቶች በየስርቻው ተወትፈው የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ ሳናዳምጥ ለንፁሃን ልንደርስላቸው ይገባል። በቅርቡ በትግራይ በተፈጠረው ችግር ትልቅ የሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል፡፡ ከጊዚያዊ ስሜት ወጥተን የምንተሳሰብበት የተቸገሩትን የምንረዳበት አብረን የምንቆምበት ከእልህ፣ ቂምና ጥላቻ ወጥተን ዘላቂውን ወደፊት ልጆቻችን የሚኖርባት አገር ስለሆነች በይቅርባይነት በመተው በመፈቃቀድ ይህንን ችግር ማለፍ እና መተሳሰብ አለብን ። በኢፈርትና በሕወሓት የንግድ ተቋማት የተከማቸው ገንዘብ የትግራይ ሕዝብ ከሰብዓዊ ቀውስ ለማዳን በ አስቸኳይ ስራ ላይ ሊውል ይገባል።#MinilikSalsawi