አዲስ አበባ በቅርስነት የተመዘገበ ጥንታዊ ቤት የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ለኦሮሚያ ፖሊስ ልዮ ኃይል ካምፕ ግንባታ ቦታውን እፈልገዋለሁ ብሎ አፍርሶታል።

 
Image may contain: house, sky and outdoorስድስት ኪሎ እቴጌ መነን ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ይገኝ የነበረው የደጅ አዝማጅ አስፋው ከበደ መኖሪያ የነበረው ጥንታዊ ቤት በቅርስነት የተመዘገበ እንደሆነ እየታወቀ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ “ቦታውን እፈልገዋለሁ” ብሎ አፍርሶታል።የቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን ከፍተኛ ኃላፊዎች ቅርስ ፈረሳውን ለማስቆም ወደ መኖሪያ ግቢው ቢደርሱ ወታደሮች እንዳይገቡ እንደከለከሏቸው ሰምተናል።
ይህ ታሪካዊ መኖሪያ ሲፈርስ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እና ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ራሱ የቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን አያውቀውም።
ኢትዮጵያ የቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፤ “ቅዳሜ እለት ወደ ውስጥ ዘልቀን በመግባት ለማስቆም ስንሞክር በወታደሮች እንዳንገባ ተከልክለን ተመልሰናል” በማለት ለሸገር ራዲዮ ተናግረዋል።
ቦታውን በባለቤትነት ለመያዝ የተዘጋጀው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ እንደሆነና ስፍራውን ለኦሮሚያ ፖሊስ ልዮ ኃይል ካምፕ ግንባታ እፈልገዋለሁ ማለቱን የጠቆሙት ፕሮፌሰር አበባው፤ በአሁን ሰዐት ሙሉ ለሙሉ ፍርስራሹን አውጥተው በመጣል ታሪካዊውን ቅርስ ጠራርገው እንደደፉት አረጋግጠዋል።
Image may contain: house and outdoorጉዳዩን አንዳንዶች “የአንድ አሮጌ ህንፃ መፍረስ” ጉዳይ አድርገው ይቆጥሩታል:: እነኚህ የቀደምቶቻችን ግብረ ህንፃዎች ግን ከባለቤቶቹ ማንነት በላይ ናቸው:: እንደሀገር የማንነት አሻራ እና የጋራ ትውስታ ማዕከል ናቸው:: ከዚህ በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችንን የቀደመውን ትውልድ ኪነህንፃ እና የግንባታ ጥበብ አንዲያጠኑ ለምርምር የምንልክባቸው መካናት ነበሩ::
ካልጠፋ ቦታ የተመዘገቡ ቅርሶች ያሉባቸውን መካናት እያሰሱ ማፍረስ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁ ይማንነት አሽራ ድምሰሳ ተግባር በመሆኑ አጥብቅን እናወግዘዋለን::
በባህል በቅርስ ጥበቃ እና በቱሪዝም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች የተመደቡ እነ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌውን እና ሠርጸ ፍሬስብሐትን የመሰሉ ባለሙያዎች ጮኸው የማይሰሙ ተቆጥተው የማያስቆሙ ከሆነ ታዲያ ለማን አቤት ይባላል? – Yohannes Mekonnen