እንጦጦ የሚገኘው የዳግማዊ ምኒልክ ቤተመንግሥት ጥገና ተጀመረ

Image may contain: cloud, house, sky, tree, outdoor and natureይህ ቤተመንግሥት አፄ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ ሳሉ እንጦጦ ላይ በስዊዝ ተወላጁና አማካሪያቸው በነበረው አልፍሬድ ኤልግ የተገነባ ነው።ከግንባታው መጠናቀቅ በኋላ ዋና ቤተመንግስታቸውን ከአንኮበር ወደ እንጦጦ ያዘዋወሩት ንጉሥ ምኒልክ ፣ ከአንዳንድ የሸዋ ተወላጆች መጠነኛ ቅሬታን አስተናግደው ነበር።
እንጦጦ የአዲስ አበባ ከፍተኛ ቦታ ነው። ዳግማዊ ምኒልክ አዲስ አበባን ሲቆረቁሩ ከአንኮበር መጥተው ያረፉበት እና ቤተ መንግስታቸውን የስሩበት ታሪካዊ ቦታም ነው።ይህ ቤተመንግስት ከአፄ ምኒልክ ሞት በኋላ ከሸዋ መኳንንት ጋር አለመግባባት የነበራቸው ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ እስከ ዕለተሞታቸው ድረስ በግዞት ያሳለፉበት ታሪካዊ ቦታ ነው።
ኮረማሽ የጉዞ ማኅበር በእርጅና ምክንያት ከፍተኛ የመፍረስ አደጋ ተደቅኖበት የነበረውን ይህን ታላቅ ቤተመንግሥት ጥገና ሥራ ለረጅም ጊዜ በheritage consortium አጥኚነት ሲካሄድ ቆይቶ የእንጦጦ ደብር ፣ የአዲስ አበባ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን እና ከበጎ ፈቃድ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የጥገና ሥራውን አንገብጋቢ ከሆነው የጣሪያ ጥገና ሥራ በትናንትናው ዕለት ተጀምሯል።
ይህንን የጣሪያ ጥገና ሥራ ለማከናወን የተወሠነ ገንዘብ ከደብሩ የተመደበ ሲሆን በቀጣይነት የግድግዳ የወለል እና የግቢ ስራዎች ይሰራሉ ።
Image may contain: outdoor and nature
Image may contain: people standing, house, sky, outdoor and nature
Image may contain: house, outdoor and nature