ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ተፈጸመ ባሉት ጥቃት አንዱ ሌላውን ከሰሱ

የሶማሌ እና የአፋር ክልላዊ መንግሥታት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለውበታል ባሉት በአዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጸመ ጥቃት አንዱ ሌላውን ወንጅለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው በሶማሌ ክልል መግለጫ መሠረት በሲቲ ዞን በአፍደም ወረዳ ሲሆን በአፋር ክልል መግለጫ ደግሞ በገዋኔ ወረዳ ነው። ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ እና እንደቆሰሉ ሁለቱም ያሉት ነገር የለም።…