በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ድባጢ ወረዳ 7 ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኝ ተናገሩ

በድባጢ ወረዳ ሰባት ሰዎች ተገድለው ሬሳቸው መገኘቱን የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት በአካባቢው “ሽፍታ ገባ” የሚል ጥቆማ እንደደረሰው አረጋግጧል። በቡለን ከተገደሉ 207 ሰዎች መካከል የስድስት ወር ጨቅላን ጨምሮ 17 ሕፃናት እንደሚገኙበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል። 43 ሺሕ በላይ ተፈናቅለዋል…