ከ60 በላይ ዜጎች በኮንሶ በማንነታቸው ምክንያት ተገደሉ #ግርማካሳ

የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ መሪ ስራውን ስላለራ መቀየር ነው ያለበት። የአንድ መሪ ወይንም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ስራው በዋናነት በቀዳሚነት የዜጎችን ደህንነትና ሰላም መጠበቅ ነው።ችግር መትከል፣ ፓርካ አስመርቆ ማስተዋወቅ፣ ወይንም ጀግና ለመምሰል መለዮ ለብሶ ፎቶ ተነስቶ መልቀቅ አይደለም።
ዶር አብይ አህመድ አራት ኪሎ ከገባ ሶስት አመት ሊሞላው ጥቂት አመት ነው የቀረው። በሕወሃት ጊዜ በ27 አመታት ካየነው የዘር ጭፍጨፋና ሰቆቃ በዶር አብይ ዘመን ባለፉት አንድ አመት ብቻ ያየነው ይበልጣል።
የሶማሌ ክልል ረስ መስተዳደር አቶ ሙስጠፊ ” በማስተዳድረው ክልል ውስጥ ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው የሚገደሉ ከሆነ እኔ ምን እሰራለሁ?” ያለውን አስተያየት ልዋስና ዶር አብይ አህመድ በሚያስተዳድረው አገር ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው የሚገደሉ ከሆነ እርሱ ምን ይሰራል?
በመተከል ያለውን ችግር በማየት ሰዎች አሻድሊ ሁሴን ለፍርድ ይቀረብ ይላሉ። ዋናው ችግር ያለው እኮ በክልል ደረጃ አይደለም ። በአገር ደረጃ ነው። የዘር ፖለቲካው፣ የዘር አወቃቀሩ፣ የዘር ሕገ መንግስቱ ነው።
የአብይ መንግስት ችግር የለበትም የሚለው የዘር ሕገ መንግስት ጣጣ ዜጎችን በየቦታው ከማንነት ጋር በተገናጨ እየጨረሰ ነው። በመተከል ያለው ችግር እስከ አሁን እልባት አላገኘም። በዚያ ያለውን ሁኔታ የሚጽፍ የሚጦምር የሚከታተል ስለሌለም በደቡብ ኢትዮጵያ ዜጎች ከማንነት ጋር በተገናኘ እያለቁ ነው።
በደቡብ ክልል፣ የኮንሶ ዞን ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በተከሰቱ ተከታታይ ግጭቶች አሰቃቂ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ከፍትኛ የአካባቢው ሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ መሄዱን ኢሰመጉ ገለጸ።
ከኅዳር 12 ቀን እስከ ኅዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም በሀይበና እና በአይዴ ቀበሌዎች፣ በአርባምንጭ፣ በጊዶሌ እና በካራት ከተማዎች ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ ቢያንስ 66 ሰዎች ተገድለዋል፣ 39 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ብዙ ቤቶችና ንብረት በእሳት ተቃጥለዋል እንዲሁም ከመቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል።