የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ዉዝግብ

የኢትዮጵያና የሱዳን ባለ ሥልጣናት ሁለቱን ሃገራት ለረጅም ዓመታት የሚያወዛግበውን የድንበር ግዛት ይገባኛል ጥያቄ ለማስወገድ ካርቱም ውስጥ ለሁለት ቀናት ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ድርድር በቀጠሮ አብቅቷል። ሁለቱ  መንግሥታት ባለፉት ሳምንታት የአንዱ ጦር ወይም ሚሊሺያ የሌላዉን ድንበር ተሻግሮ በሰዎች ላይ ጥቃት አድርሷል በማለት እየተካሰሱ ነው።…