ካለፈው ሰኔው የአርትስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በክልሉ በተከሰተው አለመረጋጋት በንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ባለሃብቶች እስካሁን ካሣ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።
በኦሮሚያ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ለማቀላጠፍ እና ባለሃብቶችን ወደ ዘርፉ ለመሳብ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት በክልሉ አስተማማኝ ፀጥታ እንዳለ የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኃላፊ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፤ ክልሉ የያዟቸው ለዘርፉ የሚውሉ ምቹ ግብዓቶች መኖራቸውን ገልጸው የኢንቨስትመንት ውል ገብተው በማያለሙት ላይ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ካለፈው ሰኔው የአርትስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በክልሉ በተከሰተው አለመረጋጋት በንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ባለሃብቶች እስካሁን በመንግሥት በኩል የተሰጣቸው ካሣ አለመኖሩን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።