በሰሜን ወሎ ወልዲያ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ ( የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ )

በሰሜን ወሎ ወልዲያ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በ145ኛ ልዩ መግለጫ የተመለከተው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ሲሆን የመብት ጥሰቱ የተፈጸመው ከሕዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 04 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ነው። ሰመጉ ባለሙያዎቹን ወደ አካባቢው ልኮ የማጣራት ሥራውን የሰራው ከየካቲት 05 እስከ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወልደያ ከተማ፣ ወልደያ ዙሪያ ወረዳ፣ ቆቦ፣ ሮቢት፣ መርሳ፣ ውርጌሳ እንዲሆም በደቡብ ወሎ ደሴ የተፈጠሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርምሮ በዚህ መግለጫ አካቷል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተሰነዘሩ17 ዜጎች እንደጠፋ እና የአካል ጉዳት እንደደረሰ ሪፖርቱ በምስል አስደግፎ አቅርቧል።

1. ሟች መምህር ታምሩ በሪሁን፡- ዕድሜ 42፣ በፌደራል ፖሊስ በጥይት የተገደለ።
2. ሟች ተማሪ ዮሴፍ እሸቱ፡- ዕድሜ 15፣ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች በጥይት የተገደለ።

3. ሟች ገብረመስቀል ጌታቸው፡- ዕድሜ 35፣ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች በጥይት የተገደለ።

4. ሟች ወ/ሮ ዝይን ንጋቴ፡- ዕድሜ 60፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭንቅላታቸውን በጥይት ተመተው የተገደሉ።

5. ሟች ንጉሴ አበበ፡- ዕድሜ 18፣ በታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ግራ ጎኑ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

6. ሟች ህጻን ዳንኤል ካሳ፡- ዕድሜ 9፣ ታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ጀርባው ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

7. ሟች ሰይድ ፍሬው ፡- ዕድሜ 31፣ በታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ልቡ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

8. ሟች መሀመድ አሰፋ፡- ዕድሜ 18፣ በታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ጭንቅላቱ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

9. ሟች ምስጋናው ይመር፡- ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከቤቱ የሞባይል ካርድ ለመግዛት እንደወጣ በመርሳ ከተማ ውስጥ በታጠቁ የመንግስት ሃይሎች በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

10. ሟች ጋሻው አወቀ፡- ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ ውስጥ በተፈጠረው ሁከት ሕይወቱ ያለፈ።

11. ሟች ናትናኤል መና፡- ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ ውስጥ በተፈጠረው ሁከት ሕይወቱ ያለፈ።

12. ሟች ሻምበል ፍትህ ርስት ፡- ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ ውስጥ በተፈጠረው ሁከት ሕይወቱ ማለፉን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል የካቲት 07 ቀን 2010 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር ወ/ጠ/ሆ/3940/10 ዓ.ም ለሰመጉ በተጻፈ ደብዳቤ ማስረጃነት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

13. ሟች አሸናፊ ሀይሉ፡- ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ ውስጥ በተፈጠረው ሁከት ሕይወቱ ያለፈ።
14. ሟች ሞላ ብርሃኑ፡- ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም በመርሳ ከተማ ውስጥ በመንግስት የታጠቁ ሃይሎች በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

15. ሟች መካን አያሌው፡- ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም በመርሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በተካሄደበት እለት በተፈጠረው ሁከት በታጠቁ የመንግስት ሃይሎች በጥይት የተገደለ።

16. ሟች ልዑል ፍስሀ፡- ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ ውስጥ በተፈጠረው ሁከት ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ወደ ተከራየው ቤት በመግባት ላይ እንዳለ በታጠቁ የመንግስት ሃይሎች በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

17. ሟች ተስፋዬ ሰጠኝ፡- ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም በመርሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በተካሄደበት እለት በተፈጠረው ሁከት በታጠቁ የመንግስት ሃይሎች በጥይት ተመትቶ የተገደለ።

ምንጭ: የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ