በአፋር ሁለት ሐይሎች ጎራ ፈጥረው ተፋጠዋል፡፡

ለ27 አመታት ተዳፍኖ የቆየ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ህዝቡ ይጠይቃል ነገር ግን ምላሽ ሠጭ አካል የለም፡፡ ህዝቡ ለመሆን ይጥራል ነገር ግን እንዳይሆን የሚፈልግ አካል ከአናቱ ተቀምጧል፡፡ አናቱ በማይድን በሽታ ተለክፈዋል፡፡ ግን ላይዲን ግማቱ ገምተዋል፡፡ የዘመናት ጥያቄ እንዳይመለስ የበላዮቹ ተፅዕኖያቸውን የቀጠሉ ሲሆን ጠያቂዎች ግን ከመጠየቅ ሳይታክቱ የወጣቱ ክፍል እየጠየቀ ነው፡፡

አሁን በአፋር ሁለት ሐይሎች ጎራ ፈጥረው ተፋጠዋል፡፡አንዱ የ27 አመት አሮጌ ስርዓት ይዞ ለመቀጥል፡፡ ሁለተኛው ግን አዲስ ትውልድ በመሆኑ አዲስ ነገር ማየት ፈልጎ ራሱን መሆን ይፈልጋል፡፡ማንነት ደግሞ ከሁሉም ቀዳሚ ነው፡፡ አሁን በነጋዴው በለውጥ ፈላጊ መካከል ቀዝቃዛ ጦርነት ተከፍቷል፡፡ እሳቱ ላይጠፋ ተያይዞ መንዳድ ግን አልቻለም፡፡ መንስኤው ደግሞ አለቃ ተብየው እጃዙር መአቀብ በማድረግ የወጣቱን ጥያቄ ለማክሸፍ እየሞከረ በመሆኑ፡፡

ብዙዎቹ የወጣቱ ክፍል የመንግሥት ደሙዝ ጥገኛ በመሆኑን የእለት እንጄራውን ላለማጣት መብቱን ማስከበር ተስኖት አጎብዳጅ ሁኖዋል፡፡ ጥቂት ቁራጦች ግን ለመቀቡ እጅ ላይሰጡ ፡ ለርካሽ ጥቅም ላያጎበድዱ ቃል ተገባብተው የትግሉ ፊታውራሬ ሁናዋል፡፡ ለማንኛውም አሁን ሜዳው ከሁለት ጎራ ሁነዋል፡፡ አንዱ ክንፍ ምንም አይነት ለውጥ አያስፈልግም በዚህ እንቀጥል የሚለው አብዴፓ እና አይሆንም ልክ እንደጎራቤቶቻችን ለውጥ ያስፈልገናል አዲስ ፊት እንፈልጋለን ማንም ይምራን አዲስ አመራር እንፈልጋለን የሚለው ወጣቱ ዱኮሂና ሌላኛው የለውጥ ናፋቂ ቡዱን ነው፡፡

ይህ ክፍል ለአገር ተስፋ፡ የነገ ጉልበት የሆነው አገር ተረካቢ የተማረ ወጣት ክፍል የያዘ ሐይል ነው፡፡ አሁን ፍጥጫው ተጧጡፏል፡፡ አብዴፓ ውድቀቱን ላለማያት ምሎ ተነስተዋል፡፡ አዲስ የካቢኔ ድልድል አድርገዋል፡፡ጥያቄው ግን አዲሱ ለውጥ በፈጣን ባቡር ላይ ያሳፍረው ይሁን ነው? ጥያቄው አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ መልካም ቀን፡፡