በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የተጣራ የባለአክስዮኖች ቁጥር 185 ሺህ ደረሰ

በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የተጣራ የባለአክስዮኖች ቁጥር 185 ሺህ መድረሱ ተገለፀ። ባንኩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የአክሲዮን ሽያጭ መጠናቀቁን እና የውክልና መስጫ ጊዜው መራዘሙን ጠቆሟል።
ቃል የተገባው 8.1 ቢሊየን ብር ሲሆን የተከፈለ የአክሲዮን ሽያጭ መጠን 6 ቢሊየን ብር መሆኑን በመግለጫው ተጠቁሟል። በሀገሪቱ የንግድ ህግም ሆነ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት አንድ የፋይናንስ ተቋም የጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ የጠቅላላ ባለአክሲዮኖች ቁጥር ምልአተ ጉባዔውን ለማሟላት አለመቻሉን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ ገልፀዋል።
ምክንያቱ ደግሞ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ባለአክሲዮኖች በውክልና ጠቅላላ ጉባኤው እንዲካሄድ ባለአክሲዮኖች ውክልና እንዲሰጡ በተጠየቁት መሠረት እስካሁን 75 ሺህ ሰው ውክልና ሰጥቷል። አቶ መላኩ ፈንታ የውክልና ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ምልአተ ጉባኤውን ለሟሟላት የውክልና አሰጣጥ ሂደቱም እስከ ታህሳስ 15/2013 ዓ.ም መራዘሙንም ገልፀዋል።