ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ «ታገቱ» የተባሉት ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም እንቆቅልሽ ሆኖ እንደቀጠለ ነዉ

መንግሥት ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ፣ ለማወቅ ለምን ተሳነዉ?

ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ አማራ ክልል ወደ ሚኖሩት ቤተሰቦቻቸው በመጓዝ ላይ ሳሉ ባልታወቁ ሰዎች «ታገቱ» የተባሉት ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም እንቆቅልሽ ሆኖ እንደቀጠለ ነዉ።

ተማሪዎቹ ታገቱ ከተባለ ከወራቶች በኋላ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጉዳዩን በቅርበትና በትኩረት እየተከታተለዉ መሆኑን ገልፆ ነበር።

የክልሉ የአደረጃጀት ዘርፍ ክፍል ስለታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ በሰጠዉ መግለጫ ጉዳዩ ያልተዘነጋና ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው ብሎ ነበር።

የታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ አንድ ዓመት ሞልቶታል። መንግሥት ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ፣ ለማወቅ ለምን ተሳነዉ? – DW

ከዩኒቨርሲቲ ሲመለሱ የታገቱ ተማሪዎችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ሰኔ 1 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር 👇👇👇

Image may contain: 7 people, text that says 'BRING BACK OUR STUDENTS #BringBack #BringBackOurStudents G00'ከዩኒቨርሲቲ ሲመለሱ የታገቱ ተማሪዎችን አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ!

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ ጠለፋውን ያቀነባበሩ፣ ያስተባበሩ እና ያሳለጡ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተማሪዎቹ እገታ “ተራ እገታ” ነው ለማለት ያስቸግራል ያሉ ሲሆን መጀመሪያ ታግቼ ነበር ብላ የተፈታችው ልጅን ጨምሮ የሌሎች ተማሪዎችንም ዶክመት የያዘ ግለሰብ በአሰሳ መገኘቱንም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ሁሉም ቀበሌዎች ከፍተኛ አሰሳ አድርገዋል፤ ተማሪዎቹ አሉ በተባሉበት ሁሉ በተደረገ አሰሳ ተማሪዎቹን በአካል ለማግኘት አልተቻለም፤ የሞተ ሰውም አንድም ሪፖርት የለም፤ ኃላፊነት የወሰደ አንድም አካልም የለም” ብለዋል።

“በቴክኒክ መረጃ የተማሪዎች ስልክ አማራ ክልል ሲገኝ፣ ጠፍቶ ደግሞ ቤኒሻንጉል ክልል ይገኛል፣ ቤኒሻንጉል ክልል ሲፈለግ ደግሞ ጠፍቶ ኦሮሚያ ክልል ይገኛል፤ ይህም እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳያል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የትኛውም ኃይል በጠለፋው ላይ ኃላፊነትን አልወሰደም፡፡ ነገር ግን፣ በምርመራው ሂደት ከክስተቱ ጋር ተያያዥነት ኖሯቸው የተገኙ ሰዎች ተይዘዋል፡፡

ተማሪዎቹን ለማስመለስ የሚደረገው ጥረት እንደ ቀጠለ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የፌደራል መንግሥት ይህንን ጉዳይ ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለቱንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ -#EBC  Via @tikvahethmagazine