ምክክሩ «የጦርነት ጭንቀት መንፈስን ለመግፈፍ» የተሞከረ ነው – የውይይቱ ተሳታፊ

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተገኘበት ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚንሥትር ጽሕፈት ቤት ጠቅሷል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ምቹ ኹኔታ እንዲፈጠር፤ የሕግ የበላይነት እንዲከበር፤ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ የሚሉ አስተያየቶች መሰጠታቸውን እና በርካታ ጉዳዮችን ማንሳታቸውንም ጽ7ቤቱ ዘርዝሯል። የውይይቱ ተሳታፊዎች የፖለቲካ አመራር ከዶይቸ ቬለ (DW)ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የነበረው ውይይት፦ «በጣም ጠቃሚ ነበር» ያሉ ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ፦ ምክክሩ «የጦርነት ጭንቀት መንፈስን ለመግፈፍ» የተሞከረ እንደኾነ የሚገልጥ አስተያየትም ተሰጥቷል። የፖለቲካ አመራር አባላቱ ስለ ውይይት መድረኩ አስተያየታቸውን እንዲያካፍሉ በመጠየቅ የአዲስ አበባው ዶይቸ ቬለ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል።