በአክሱም ከተማ የዘንድሮው የህዳር ጽዮን በዓል አከባበርና የህወሃት ካድሬ “ካህናት”

 

ከሊቃውንት አባቶቻችን የተማሩት በሊቃውንት አበው መንገድ የሚያቀርቡት ትምህርት የጥንቷን የዛሬዋንና የነገዋን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ትክክለኛ ማንነቷን ያሳያል። እባካችሁ ቤተ ክርስቲያናችን በጉባዔዋ በለዛዋና በስልቷ የማትወክላችሁ ጭምብል ለባሾች እንወክላለን ብላችሁ አትቅረቡ። መዕመናንም ጭምብል ለባሾችን ከቤተ ክርስቲያናችን ጋራ በማያያዝ እያቀረባችሁ ቤተ ክርስቲያናችንን የማይመጥን ነገር አታሰራጩ።

በዘንድሮው የህዳር ጽዮ በዓል አከባበር ላይ ታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት መነሻ የሆነችው አክሱም ውስጥ ምን ተፈጸመ? ለነፍሳቸው ሳይሆን ለህወሃት ያደሩ ካህናት ምን የማይረሳ ነገር ፈጸሙ? በዚህ ዓመት በ 2013 አክሱም ውስጥ የተከበረውን የህዳር ጽዮንን እንዴት እንዳከበርነው እንዴት እንዳሳለፍነው የሚዘግበውን አቀረብንላችሁ።