ሁለቱ የፖሊስ ባለስልጣናት ያልተናበቡበት መረጃ – 38 የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው

ሁለቱ የፖሊስ ባለስልጣናት ያልተናበቡበት መረጃ
  • – 38 የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል። – የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም( በዘገባ ላይ ያለዉ መላኩ ፈንታ የስም ስህተት ብቻ መሆኑን እየገለጽን .. ዜናዉ የተጓደለ መረጃ የለውም – ኢትዮ ኤፍ ኤም)
  • – 38 የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው። – የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጀላል አብዲ ለሸገር
  • ኢትዮ FM በበኩሉ “በዘገባ ላይ ያለዉ የስም ስህተት ብቻ መሆኑን እየገለጽን ይህን የተናገሩት ም/ኮ ዘላለም መንግስቴ መሆናቸዉን እያሳወቅን ለተፈጠረዉ የስም ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ከዚህ ዉጭ ግን ዜናዉ የተጓደለ መረጃ የለውም” ብሏል።
———————————————-
38 የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
38 የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ለሸገር ተናገረ፡፡ በዛሬው ዕለት አንድ የግል FM ሬዲዮ ጣቢያ Ethio FM እና በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ሰበር ዜና በሚል 38 የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ ብለው ዘግበዋል፡፡
ሸገር ይህንኑ መነሻ አድርጎ የፌዴራል ፖሊስን የጠየቀ ሲሆን መረጃው ሀሰት መሆኑ የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ጀላል አብዲ ነግረውናል፡፡ – ሸገር
———————-
የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ⬇️⬇️⬇️
38 የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት እስካሁን በተወሰደው የህግ የበላይነት የማስከበር ስራ 38 የህወሃት አመራሮች በህግ ጥላ ስር ውለዋል።
ይሁንና ምክትል ኮሚሽነሩ እነማን በህግ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አልተናገሩም።
እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ 298 የህወሀት አመራሮች ላይ ምርመራ ለማድረግና በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበራ ለማድረግ ትዕዛዝ ተላልፏል። ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
———————————————————————————
Image“38 የህወሃት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ” የሚል ዜና ዛሬ በስፋት ተሰራጭቷል።
የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ዛሬ ለኢትዮጵያ ቼክ እንዳሳወቁት ተያዙ ተብለው በሚዲያዎች የተጠቀሱት ግለሰቦች በትግራይ ክልል የሚገኙ “ዋናዎቹን የህወሃት ሰዎች” የተመለከተ አይደለም።
ም/ኮ ዘላለም እንደገለጹት በሚድያ የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ከሳምንታት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ እና ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት በመከታተል ላይ የሚገኙ ናቸው፣ ከሰሜን ዕዝ ጋር የሚደረገውን የሬዲዮ ግንኙነት እንዲቋረጥ ያደረጉ ይገኙበታል ብለዋል።