የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን አጠናቀቀ

በምስረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን አጠናቀቀ!

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በምስረታ ሂደት ላይ በቆየበት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ160 ሺህ በላይ አክሲዮኖችን፤ ከሰባት ቢሊዮን በላይ ብር ሽያጭ መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ከአምሰት ቢሊየን በላይ ብር ደግሞ በካፒታል መሰብሰቡንም ገልጿል። በዚሁ ወር መጨረሻ ደግሞ ከባለአክሲዮኖች ጋር ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘነው መረጃ ያሳያል።