በጋሞ ጎፋ ዞን ምእራብ አባያ ወረዳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን አመራር የሚደግፉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው።

በጋሞ ጎፋ ዞን ምእራብ አባያ ወረዳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን አመራር የሚደግፉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው። የደረሰኝ ሙሉ መረጃ ይኸው 👉 ማሕሌት ፋንታሁን


“ምዕራብ ዓባያ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መስተዳድር፥ በጋሞ ጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች አንዷ ናት። በወረዳዋ ውስጥ የሚገኙ የዶ/ር አብይ አህመድ ደጋፊዎች “ለውጥን እንደግፍ፥ ዴሞክራሲን እናበርታ” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ለማካሄድ ኮሚቴ አዋቅረው በህጋዊ ደብዳቤ (የኮሚቴዎችን ስም ዝርዝርና ኋላፊነት እንድሁም በዕለቱ ስለምከናወኑ ተግባራት ዝርዝር የያዘ) የወረዳውን አስተ/ር በመጠየቅ የወረዳው አስተ/ርም አዎንታዊ ነልስ ለኮሚቴው በመስጠት የድጋፍ ሰልፉ በቀን 24-11-2010 ዓም (ማክሰኞ ዕለት) እንደሚካሄድ ከተስማሙና ለዝግጅቱም አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅቶች (ባንድራዎችን መስፋት፥ ለህብረተሰቡ የቅስቀሳ ሥራ፥ ወዘተ) እየተደረጉ ባሉበት ወቅት ከቀናት ልዩነት በኋላ የወረዳው አስተ/ር የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪ ክኮሚቴዎችን ዳግም በማስጠራትና በመሰብሰብ የድጋፍ ሰልፉን እንደከለከሉ አስታወቃቸው። ለዝህም እንደምክንያት የተጠቀሰው ወረዳዋ የድጋፍ ሰልፉ ከተፈቀደ በኋላ የስጋት ቀጠና ሆናለች በሚል ከዞን የመጡ አመራሮች የጋሞ ጎፋ ዞን አስተ/ር አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ እንድሁም የፀጥታ መምሪያ ኋላፊው አቶ ቤታ አንጁሎ ወደ ወረዳዋ ድረስ በመምጣት የድጋፍ ሰልፉን ከልክሉ ብለውናል የሚል ነው (የወረዳዋን ወቅታዊ ሁኔታ ከዞን አመራሮች በላይ እንደሚያውቅ እየታወቀና ችግሮች ብኖሩም እንኳን እችላለሁ ብሎ የወረዳው አስተ/ር ከፈቀደ በኋላ ለዞን አመራሮች ቅድሚያ በመስጠት ከሕዝቡ ተቀንሷል)።
ስለሆነም በነዝህ ቀናቶች ውስጥ ስለድጋፍ ሰልፉ ቅስቀሳ በፌስቡክ ቀስቅሳቿል፥ በፌስቡክ አመራሮችንና ባለሀብቶችን ሰድባችኋል፥ የቀን ጅብ ብላችኋል ተብለው እንድሁም ኮከብ የሌለውን ህገ-ወጥ ባንድራ ሰፍታችሁ ለሕዝብ አከፋፍላችኋል፡ ይህን የሚያስደርገው ዶ/አብይ ማን ነው? እኛ ኢህአዴግ እንጅ ዶ/ር አብይን አናውቅም በሚል በወረዳው አስተ/ር አቶ አብርሃም አይካ፥ በፍትህ ጽ/ቤት ኋላፊ አቶ እስራኤል አየለ፥ በፀጥታ ኋላፊው አቶ ቶማስ ቶቸ፥ በፖልስ አዛዥ፥ በድርጅት ኋላፊ አቶ ሙላቱ፥ በስቭል ሰርቭስ ኋላፊ አቶ ያቺሶ ያያ እና የወንጀል መከላከል ሥራ ሂደት አስተ/ሪ በጋራ ባሳደሩት ጫና 6 ልጆች ተይዘው በወራዳዋ ፖልስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ። እነዝህን 6 ልጆችን” ዝርፊያ ለማካሄድ ቡድን እያደራጁና ሕዝብ እያነሳሱ ነበር በሚል የምርመራ ሥራ ሂደት አስተባባሪ ሳጅን አባይነህ መስቀል ያለምርመራ መዝገብ ከመርማሪ ፖሊስ ጋር የላከውን ጉዳይ ፍ/ቤቱ በአግባቡ ሳይመረምር በመርማሪ ፖሊስ የተጠየቀውን 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ በሙሉ በመፍቀድ ልጆቹ በደረቅ ፖልስ ጣቢያ እንድቆዩ አድርጓል። በፖልስ ጣቢያ በጊዜ ቀጠሮ የሚገኙ ወጣቶች የሚከተሉ ናቸው፡
1ኛ- ካሣሁን ባንቴ
2ኛ- ታገል ላቆ
3ኛ- ስርጋዊ የማነ
4ኛ- አሸናፊ በቀለ
5ኛ- እስራኤል በጋሻው እና
6ኛ- ተገኝ ኡቼ ናቸው።
በመሆኑም የመናገር መብታቸውን የሀሳብ ነፃነትን ተጠቅመው ለተናገሩት የተወሰደባቸው እርምጃ (ፖልስ ጣቢያ ውስጥ ድብደባ የተፈፀመባቸው አሉ) ህገ-ወጥ በመሆኑ የአካል ድኅንነት መብታቸው እንድከበርና ተገቢውን ፍትህ እንድያገኙ እንጠይቃለን።
ፍትህ ለምዕራብ ዓባያ ወጣቶች።”