ዘመቻው በጥቂት ቀናት ይጠናቀቃል – የጠ/ሚ አብይ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ

የጠ/ሚ አብይ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ አሁን ላይ አብዛኛው የትግራይ ክፍል በመከላከያ ስር መሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መቐለ ናት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ያልሆነችው፣ ዘመቻው በጥቂት ቀናት ይጠናቀቃል ብለዋል።

በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው ወታደራዊ ግጭት ሦስት ሳምንት ሊሆነው ተቃርቧል። መንግሥት ሕግ ማስከበር በሚለው ወታደራዊ እርምጃ ጋር ተያይዞ የሽምግልና ጥያቄዎች፣ በግጭቱ ስለተፈናቀሉ ሰዎች፣ ከማንነት ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ እስሮችና ሌሎችም ጉዳዮች እየተነሱ ነው።

የቢቢሲዋ ካትሪን ባይሩሃንጋ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ጋር ባደረገችው ቆይታ በርካታ ጥያቄዎችን አንሰታላቸዋለች።

ቢቢሲከሰሞኑ ዜና እንጀምር፤ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ የፌደራል መንግሥትና የህወት አመራሮችን እንዲያሸማግሉ በሚል ስት የቀድሞ መሪዎች የአፍሪካ ብረት ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሰየማቸውን አስታውቀዋል። የሊቀ መንበሩ መልዕክት ልዑካኑ አዲስ አበባ የሚመጡት ሊያሸማግሉ ነው ቢልምኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን ድርድርም እንደሌለ ተገልጿል። ይ ልዩነት እንዴት መጣ?

አቶ ማሞ በዋነኝነት አፍሪካውያንን ወንድማቾቻችንና እህቶቻችን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የተፈጠረባቸውን ስጋት መግለፃቸው የተለየ ነገር አይደለም፤ ስጋታቸውንም እንረዳለን። ይሄንንም ሁኔታ ያው የተለመደው የዲፕሎማሲ አካል አድርገን ነው የምናየው።

ነገር ግን ለአህጉራዊ ድርጅታችን እንዲሁም ለሊቀ መንበሩ ካለን ክብር አንፃር ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ልዑካኑን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ እናስረዳቸዋለን፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርድሩን አይቀበሉትም።

በይፋ እንደተነገረውም ይህ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አንድ በአንድ የሚደረግ ስብሰባ ነው።

ቢቢሲ፡ ልዑካኑ ሁለቱን አካላት ለማሸማገል ከመሰየማቸው አንፃር ትግራይ በመሄድ ከህወት አመራር አባላትም ጋር መገናኘት ይፈልጉ ይሆናል። ልዑካኑ ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ትፈቅዱላቸዋላችሁ?

አቶ ማሞ፦ የልዑካኑን የወቅቱን ጉብኝት በጥልቀት መረዳት ያስፈልጋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ጋር ለመነጋገር ብዙ ጥረት አድርጓል። በኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ላይ መምከር የሚያስችሉ ገንቢ ውይይቶችንም ለማድረግ ሞክሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተደጋጋሚ ከትግራይ ክልል አስተዳደር ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ቢቢሲ፦ እዚህ ጋር ላቋርጥዎትና፤ ልዑካ ሁለቱን አካላት የማናገር ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። ሆኖም ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች ቆመዋል። ታዲያ ልዑካኑ ወደ ትግራይ በመሄድ በግጭቱ የሚሳተፈውን ሌላኛውን ወገን ማግኘት ይችላሉ?

አቶ ማሞ በትግራይ ክልል ያለው ሕገወጥ አስተዳደር ጋር ያለው የፖለቲካ ልዩነት አይደለም። ይሄ ሕግን የማስከበር ዘመቻ ነው። በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው አለመረጋጋት ተጠያቂ ወይም ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረግ ነው። ከወንጀለኞች ጋር አንደራደርም። ወደ ፍትህ ማምጣት ነው አላማችን፤ ድርድር የሚባል ነገር የለም። መንግሥትም በተደጋጋሚ የሚገልፀው አቋሙ ይህ ነው።

በእኔ አስተሳሰብ አፍሪካውያን ወንድምና እህቶቻችን ህወሓት እጅ እንዲሰጥ ጫና ቢያደርጉ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ፤ ተጠያቂም ሊሆኑ ይገባል። ለወንጀለኞች ድርድር ሳይሆን ተገቢው ነገር ወደ ፍትህ ማምጣት ነው።

ቢቢሲ፡ ልዑካኑ ወደ ትግራይ ክልል እንዲሄዱ ካልተፈቀደላቸውና ከህወት አመራር አባላት ጋር ውይይት ማድረግ ካልቻሉ የሚሉትንስ ነገር እንዴት ማከናወን ይችላሉ? ወደ መጀመሪያ ጥያቄዬ ልመለስና ልዑካኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ካናገሩ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል እንዲሄዱ ይፈቀድላቸዋል ወይ?

አቶ ማሞበትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ወታደራዊው ዘመቻ በቅርቡ ይቋጫል የሚል እምነት አለን። መንግሥት የሚያደርገው ሕግ የማስከበር ዘመቻ በቅርቡ ከተጠናቀቀ፣ በአገሪቱ አለመረጋጋት ላይ እጃቸው ያለበት የህወሓት አመራሮች ግጭቱ እንዲያቆም ከፈለጉ ማድረግ ያለባቸው ነገር ቢኖር እጃቸውን መስጠት ነው። ይህንን ለማድረግም ሆነ ለህወሓት አመራር አባላት አቋሙን ግልፅ ለማድረግ የትኛውም አካል ቢሆን ትግራይ ክልል መሄድ አያስፈልገውም።

ቢቢሲ፦ ስለዚህ የሚሉት ለአሁኑ ልዑካኑ ወደ ትግራይ ክልል መሄድ አይችሉም ነው?

አቶ ማሞ፦ እንዳልኩት ልዑካኑ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ለማግኘት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም እየተደረገ ስላለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ያስረዷቸዋል።

ቢቢሲ፦ ወታደራዊውዘመቻ በትግራይ ዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም በማለት የፌደራል መንግሥት ይገልፃል። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በግጭቱ ምክንያት በርካቶች ተፈናቅለዋል። የተለያዩ የሰብዓዊ ድርጅቶችም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉና ችግር ውስጥ ያለውን የትግራይ ዝብ ለመርዳት የሚያስችል መተላለፊያ እየጠየቁ ነው። ሆኖም መንግሥት ድርጅቶቹ ወደ አካባቢው በመግባት ሰላማዊ ሰዎችን እንዲረዱ ፍቃድ አልሰጠም እያሉ ነው። ለምንድን ነው ይህ የማይፈቀድላቸው?

አቶ ማሞ፦ አንዳንድ ነገሮችን ግልፅ ላድርግ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ሕግን የማስከበር ዘመቻ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም። በተጨማሪም ይህ ዘመቻ ሁሉንም የህወሓት አባላትን የሚመለከት ሳይሆን በህወሓት ውስጥ ያሉ ወንጀለኞች ላይ ያነጣጠረ ነው። ይሄ ለሁሉም ግልፅ መሆን አለበት።

በእነዚህ የህወሓት አመራሮች መወገድ የትግራይ ሕዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለሌላው ሕዝብ እንደሚጨነቀው ሁሉ ለትግራይ ህዝብም ያስባል። ጥያቄውንም ለመመለስ በተቻለው መጠን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሕዝቡ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያደርግም የቻልነውን እያደረግን ነው።

በርካታ የትግራይ ክፍሎችም በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ናቸው። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት በአብዛኛው የትግራይ ክፍል የሚያስፈልገውን እርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አብሮ ይስራል። በአሁኑ ወቅት መቀለ ብቻ ናት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ያልሆነችው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ነፃ ከሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የሰብዓዊ እርዳታን ለሕዝቡ ለማቅረብ የመስራት እቅድ አለው። በዚህም በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉትም ሆነ ወደ ጎረቤት አገራት ለተሰደዱ ኢትዮጵያውያን የሚደርስ ይሆናል።

ቢቢሲ፦ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ሰብዓዊ ድርጅቶች ሰላማዊ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦት ለመድረስ የሚያስችል መተላለፊያ እንዲኖር እየጠየቁ ነው። ድርጅቶቹ እርዳታ ለማድረስ ማዕከላዊው መንግሥት የሚያስፈልገውን ሊያመቻች አልቻለም እያሉ ነው።

አቶ ማሞይሄ ትክክል አይደለም። ይህንን በሁለት መንገድ ልናየው ይገባል። ነፃ ባወጣናቸው አካባቢዎችና በመከላከያ ስር ባሉ አካባቢዎች መንግሥት በአሁኑ ወቅት የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እየሰራ ነው። ለአካባቢው ነዋሪ ምግብ፣ መጠለያና መድኃኒት ለማቅረብ ከተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር እየሰራ ነው።

ለምሳሌም ያህል አርብ ዕለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካንን የያዘ ቡድን ወደ ትግራይ ክልል የላከ ሲሆን ይህም በተለያዩ አካባቢዎች የሚያስፈልገውን ቁሳቁሶችና አቅርቦትም ለመረዳት ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር አንሰራም የምንልበት ምክንያት የለንም።

በመከላከያ ስር ባልሆኑት አካባቢዎች ጋር ስንመጣ ሰላማዊ ሕዝቦች የሚጠበቁበትን መንገድ ለማረጋገጥም ጦሩ እየሰራ ነው። ይህ ወታደራዊ ዘመቻ ያልተቋጨበት ዋነኛ ምክንያትም መንግሥት ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ በመስራቱ ነው። መንግሥት በመከላከያ ስር ባሉትም ሆነ ባልሆኑትም አካባቢዎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር ይሰራል።

ቢቢሲ፡ በግጭቱ ሰላማዊ ዝብ እንዳይጎዳ እየሰራን ነው እያላችሁ ነው። ሆኖም በወታደራዊው ዘመቻ የአየር ጥቃት፣ ሮኬትና ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላኖች) እየተጠቀማችሁ ነው። እንደዚህ አይነት ውጊያዎች ነጥሎ የመምታት አካሄዶች አይደሉምና በርካታ ንፁሃን ሰዎችም እየሞቱ ነው፤ ጉዳትም እየደረሰባቸው ነው።

አቶ ማሞ፦ ይሄ ግጭት እንደመሆኑ መጠን ጉዳት መድረሱ አይቀርም። ሆኖም ለመከላከያ ኃይሉ የተላለፈለት ጥብቅ ትዕዛዝ ቢኖር ወታደራዊውን ዘመቻ በተቻለ መጠን ንፁሃን ዜጎችን በመጠበቅ ቅድሚያ እንዲሰጡ ነው። የሰላማዊ ዜጎች ደኅንነትና ጥበቃ ለወታደራዊው ዘመቻው ቁልፍ ጉዳይ ነው። መንግሥት ለንፁሃን ዜጎችም ከፍተኛ ኃላፊነት ስላለበትም ነው ህግ የማስከበር ዘመቻው ይህንን ያህል የወሰደው። ያለበለዚያ በሳምንት ውስጥ ይጠናቀቅ ነበር።

የተነሳው የአየር ጥቃት ጉዳይ በዋነኝነት ኢላማው ወታደራዊ ማዕከላትንና የጦር መሳሪያ ቁሳቁሶችን ነው። ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ አያደርግም። ያንንስ ለምን እናደርጋለን? የትግራይ ሕዝብ ዜጋችን ነው። ዘመቻውን የምናድርገው ህፃናትን፣ የዕድሜ ባለፀጎችንና ሌሎችንም ሰላማዊ ሰዎችን በማይጎዳ መልኩ ነው።

ቢቢሲ፦ ይሄን ግጭት አስቸጋሪና ፈታኝ የሚያደርገው መሬት ላይ እየተፈጠረ ስላለው ጉዳይ መረጃ ማግኘትና ማጣራት አለመቻል ነው። የትኛውም አይነት የመገናኛ ዘዴ መቋረጡ እንዲሁም ጋዜጠኞች በቦታው እንዳይገኙ መደረጉ ምን እየተከናወነ ነው? የሚለውን ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል። ለምንድን ነው ከቀሪው ለም መለየት ያስፈለገው? በትግራይ እየተከናወነ ስላለው ቀሪው ለም እንዳያየው የማትፈልጉት ጉዳይ ምንድን ነው?

አቶ ማሞ፦ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት እፈልጋለሁ። የመገናኛ ዘዴው በተወሰኑ አካባቢዎች የተቋረጠው ህወሓት ራሱ የመገናኛ ልማቱን ለራሳቸው ወታደራዊ ዘመቻ ሲሉ የተወሰነውን በማውደማቸው ነው። ይሄ አንደኛው ምክንያት ነው።

ሌላኛው ምክንያት ትግራይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመሆኗ ወንጀለኛ ቡድኖች ጥቃት እንዳያደርሱና የተለያዩ ቡድን አባላትንም በማነሳሳት በተለያዩ አገሪቷ ክፍል አለመረጋጋትን እንዳይፈጥሩ ለማድረግ መከላከያው እንደዚህ አይነት እርምጃ ሊወስድ ይችላል። ይሄ ካሁን በኋላ ጉዳይ አይሆንም ምክንያቱም ቀደም ብዬ እንዳልኩት አብዛኛው የትግራይ ክፍል በመከላከያ ስር ሆኗል። በሚቀጥሉት ቀናትም ጋዜጠኞች ወደ ክልሉ የመሄድ እድሉ ይኖራቸዋል።

ቢቢሲ፦ በትግራይ እየተካሄደ ባለው ነገር ተጠያቂ ላለመሆንና ግልፅነትን በመሸሽ አይደለም? አገሪ ውስጥ ግጭት ሲፈጠር ኢንተርኔት መዝጋት ለኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አይደለም። በኦሮሚያም ላይ የተከሰተውን አይተነዋል። መንግሥት ምርመራ በማይፈልግበት ወቅት ሰዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንዳያውቁ የማድረግ ሁኔታም ነው።

አቶ ማሞ በዚህ አባባል አልስማማም። እንዳልኩት ይህ ወታደራዊ ዘመቻ ነው። የወታደሩን የየቀን እቅድና አፈፃፀም መናገር አልችልም። ግን ከዚህም ጋር ተያይዞ መከላከያው እርምጃውን የተሳካ ለማድረግ ማንኛውንም ዘዴ የመጠቀም መብት አለው። ሆኖም ወደ ነጥቡ ስመለስ ምንም መደበቅ የምንፈልገው ነገር የለም።

የክልሉ ደኅንነት ከተረጋገጠ፣ ሕግና ሥርዓት ከተመለሰ በኋላ ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ክልል መጥተው መጎብኘታቸውን በደስታ የምንቀበለው ጉዳይ ነው። ምርመራም ሆነ ተጠያቂነቱ በህወሓት ላይ ነው መኖር ያለበት። ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የንፁሃን ጭፍጨፋ የተፈፀመው በህወሓት ነው። ጋዜጠኞች ይህንን ሄደው ሊመረምሩ ይገባል። የአካባቢውንም ነዋሪ ሊያነጋግሩ ይገባል።

ምንም የምንደብቀው ነገር የለም። ወታደራዊው ዘመቻ እየተካሄደ ያለው ሕጋዊ በሆነ መንገድ፣ ለንፁሃን ዜጎች ቅድሚያ በመስጠት ነው። ከመንግሥት በኩል የምንደብቀው ጉዳይ የለም።

ቢቢሲ፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፤ በማንነታቸው ብቻ ለእስር ተዳርገዋል እየተባለ ነው አንዳንዶቹም ያሉበት አይታወቅም። ከዚህም በተጨማሪ በማንነታቸው ቤቶቻቸው እንደተፈተሹ፤ እንዲሁም በብራቸው እየተነጠሉ እየተጠቁ እንደሆኑ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ይህ አንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም የምትሉ ከሆነ፤ እንዴት ይታያል?

አቶ ማሞ፦ ይህ መንግሥት መቼም ቢሆን በብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን አይሰነዝርም። በብሔር አይነጥልም። በጣም የሚገርም ነው። ህወሓት ነው ብሔርን መሰረት ያደረገ ሥርዓት የፈጠረው። መንግሥት እያደረገ ያለው ነገር ማኅበረሰቡ እኩል በሆነ መንገድ የሚተሳሰርበትን ራዕይን የመፍጠር ሥራ ነው እየሰራ ያለው። በምንም መንገድ ቢሆን መንግሥት ዜጎችን ትግራዋይ በመሆናቸው ኢላማ አያደርግም።

የትኛውም የሕግ ማስከበር እየሰራን ያለነው መረጃን በተመረኮዘ መልኩ ነው፤ ግለሰቦቹ ያላቸውንም ግንኙነትም በማየት የተጠና ነው። ግን ያው ግጭት እንደመሆኑ መጠን ወንጀል ተፈፅሞ ሊሆን ይችላል የሚሉ መረጃዎች ሊወጡ ይችላሉ። ሕዝቡ የተጠራጠሯቸውን ወንጀሎች ሊያሳውቅ ይችላል። በዚህ አጋጣሚ የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። እነዚህን እርምጃዎችንም በምንወስድበት ወቅት በተገቢውና በተጠና መልኩ ለማድረግ እንሞክራለን።

ህወሓት ብሔርን መሰረት ያደረገ ፓርቲ ከመሆኑ አንፃር በርካታ አባላቶቹ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ከውጭ ሲታይ መንግሥት አንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ ወይም ኢላማ ያደረገ ይመስላል። ነገር ግን ከፀጥታ ኃይሉ አባላት መካከል ክፍተት ካለ ማስተካከያዎችን እንወስዳለን። ከሕዝቡ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን እያደረግን ነው። ሕዝቡ ቅሬታውን የሚያሰማበትን ማዕከላት እያቋቋምን ነው። ቅሬታዎችን ስንሰማም ማስተካከያዎችን እናደርጋለን።

ኢ-መደበኛ በሆኑ መልኩ የሚገኙ መረጃዎችንም የማጣራት ሥራም እንሰራለን። ችግሮች ካሉ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንወስዳለን። ነገር ግን በእርግጠኝነት የምናገረው መንግሥት በተቀናጀ መልኩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እርምጃዎችን አይወስድም። ይህ ዘመቻ በተወሰኑ የህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው እንጂ በሕዝቡ ላይ አይደለም።

ቢቢሲ፦ ወታደራዊው ዘመቻ በተወሰኑ የህወት አባላት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን በትግራይ ክልል አካውንታቸውን የከፈቱ ሰዎች እንዲታገድ ተደርጓል። በአየር መንገዶች ብሔርለመለየት ራዊ መታወቂያ እየተጠየቅን ነው የሚሉ አሉ አንዳንዶችም በማንነታችን መሰረት ተደርጎ እንዳንጓዝ ተደርገናል ይላሉ። ከትግራይ ዝብ ጋር ግንኙነት ስለማጠናከር እየተነገረ ይህ ሁኔታ መነጠል አይሆንም? ምንም እንኳን ጦርነቱን ብታሸንፉም ዝቡን የምታጡበት መንገድ አይፈጠርም?

አቶ ማሞለፀጥታ ኃይሎች ግልፅ የሆነ ትዕዛዝ ነው የተላለፈላቸው። የፀጥታ ኃይሉ ባገኘው መረጃ መሰረት ተመርኩዞ እርምጃ እንዲወስድ ነው። ብሔርንና ማንነትን መሰረት ያደረጉ ነገሮችን እንዲህ በቀላሉ የምናየው አይደለም። የምናወግዘውም ጉዳይ ነው። በጭራሽ ይሄ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው።

ሆኖም ከተለያዩ የተሳሳቱ መረጃዎች ልንጠነቀቅ ይገባል። ለምሳሌ ከጥቂት ቀናት በፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ 50 ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች በአዲስ አበባ ታስረዋል የሚሉ መግለጫዎች ወጥተዋል። ይሄ ከእውነት የራቀ መረጃ ነው።

ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ300 ያነሰ ነው። ሁሉም ደግሞ ከትግራይ አይደሉም። ከእነዚህ ውስጥ በርካቶቹ ግለሰቦች የታሰሩት ሕገወጥ መሳሪያ በመያዝ ነው። በጣም ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ሐሰተኛ መረጃዎችን የመንዛት ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው።

ከመረጃ ጋር ባልተያያዘ የማንንም ባንክ አካውንት አላገድንም መንግሥት ያገደው የባንክ አካውንት ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸውን የተወሰኑ ተቋማትን ነው። ከዚህ በተለየ የትግራይ ተወላጆች ባንክ አካውንት አልታገደም። ይሄ ከእውነት የራቀ ነው።

ቢቢሲ፦ የተሳሳቱ መረጃዎችን ሲያነሱ መንግሥት ራሱ ሰተኛ መረጃዎች እንዲሰራጩ የሚያደርግ ሁኔታን ፈጥሯል። ጋዜጠኞች በተለያዩ አካባቢዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መዘገብ አይችሉም። ጋዜጠኞችም እየታሰሩ ነው። በትግራይ ያለው የመገናኛ ዘዴም ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል

አቶ ማሞ የመገናኛ ዘዴው የተቋረጠው በትግራይ ክልል ብቻ ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ጋዜጠኞች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መዘገብ ይችላሉ። ሙያው የሚጠብቅባቸውን ግዴታዎችን ማሟላት አለባቸው።

የተለያዩ አገራት ሪፖርተሮችም በአዲስ አበባ በየቀኑ እየሰሩ ነው። የመገናኛ ዘዴው ሙሉ በሙሉ የተቋረጠው በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ነው። እንዳልኩት ወታደራዊው ዘመቻ ከተጠናቀቀ በኋላ ጋዜጠኞች ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

ቢቢሲ፦ የመጨረሻ ጥያቄ በአየር መንገድ የቀበሌ መታወቂያ ማሳየት ለምን አስፈለገ?

አቶ ማሞ፦ለሁሉም ያ አይመስለኝም። የደኅንነት ሠራተኞች በመጀመሪያ አካባቢ የተወሰኑ ሰዎችን መታወቂያ እንዲያሳዩ ያገኙትን መረጃ ተመርኩዘው ጠይቀዋቸው ይሆናል። ይህንንም የሚያደርጉት የሰዎችን መሰረታዊ መብት በጠበቀ መልኩና የመንቀሳቀስ መብታቸውን በማይጋፋ መልኩ ነው። ይሄ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ አይደለም።

ቢቢሲ፦ መንግሥት መቼ ነው መቀን ለመቆጣጠር የሚያስበው? ከዚያ በኋላስ ምን ይፈጠራል?

አቶ ማሞ የመንግሥት ሕግን የማስከበር ወታደራዊ ዘመቻ በተያዘለት እቅድ እየተከናወነ ነው። የመከላከያ ኃይል በርካታውን የትግራይ ክፍልን ተቆጣጥሯል። ከእነዚህም መካከል ዋነኞቹ ከተሞች ለምሳሌ አድዋ፣ አክሱምና አዲግራት ይገኙበታል። በመከለከያ ስር ያልሆነችው ዋና ከተማዋ መቀሌ ብቻ ናት። በቅርቡም እንደሚጠናቀቅ እንጠብቃለን።