ጀርመን ለጦር ሀይሎች ሆስፒታል 1 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ይህ ድጋፍ ወደፊትም እንደሚቀጥልና ወታደራዊ ግንኙነታችን ማሳያ ነው – የጀርመን መከላከያ ሰራዊት ቴክኒካል አማካሪ ቡድን ሀላፊ ኮ/ል አንደሬ ስኮፊስ 
የጀርመን ኤምባሲ ለጦር ሀይሎች ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 1 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ፡፡
የሆስፕታሉ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት መምሪያ ሀላፊ ብ/ጀ ይልማ መካንንቴ ፣ የተደረገው ድጋፍ ለሆስፒታላችን አገልግሎት አሰጣጥ እጅግ ፋይዳቸው የጎላ ነው ፡፡ ይህም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል ፡፡
የጀርመን መከላከያ ሰራዊት ቴክኒካል አማካሪ ቡድን ሀላፊ ኮ/ል አንደሬ ስኮፊስ ፣ ይህ ድጋፍ ወደፊትም እንደሚቀጥልና ወታደራዊ ግንኙነታችን ማሳያ ነው ብለዋል ፡፡