ፍትሕ ታሸንፋለች፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሐሰተኛው አጥፊ ቡድን መጨረሻ ተቃርቧል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

በትግራይ ክልል የሚካሄደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ ደግሞም ሀገራችንን በመዝረፍ እና ሰላሟን በማወክ የተሰማሩትን ተጠያቂ በማድረግ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ህብረት የሚሆን ጠንካራ መሠረት እንገነባለን ሲሉ ገልጸዋል።
በተለይም ባለፉት ቀናት የታዩት ሁኔታዎች በሕወሓት ውስጥ ያለውን አጥፊ ቡድን ትክክለኛ ማንነት የገለጡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
በሰብአዊነት እና በሰላም ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉ ተጠያቂዎች ይሆናሉ። ፍትሕ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባለን ውሳኔ በቆራጥነት እንገሠግሳለን ብለዋል።
በሴቶች እና በወንዶች ልጆቿ ጽናት እና ቆራጥነት፣ ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነት የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት ታጠናቅቃለች ሲሉም ገልጸዋል።
Image