የህወሓት የጥፋት ቡድን ያሰለጠናቸዉ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች ሲጠቀሙበት የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት የጥፋት ቡድን ያሰለጠናቸዉ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች ሲጠቀሙበት የነበረ የጦር መሳሪያ በሁመራ ከተማ ተያዘ፡፡
በሁመራ ከተማ ሕወሓት ያሠለጠናቸዉ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች ሲጠቀሙበት የነበረ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታወቀ።
በሁመራ ከተማ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታትን ለመቃወም የሕወሓት ጁንታ ሲያሠለጥናቸው የቆዩ ቡድኖች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች የመከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ እንዲሁም የአካባቢዉ ሚሊሻ በወሰዱት ሕግ የማስከበር ተግባር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።
 –
የተያዙት የጦር መሳሪያዎች የኢትዮጵያንና ኤርትራ መንግስትን ለመቃወም የህወሓት የጥፋት ቡድን ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ቡድኖች ሲጠቀሙ የነበሩባቸው የተለያዩና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ መሆናቸውን ከመተማ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ፖሊስ እና የአካባቢዉ ሚሊሻ በወሰዱት ህግ የማስከበር ተግባር የጦር መሳሪያዎቹ መያዛቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰዉ ተናግረዋል፡፡