ጀግናው ሠራዊታችን ሁመራንና ዋናውን መስመር ተከትሎ እስከ እንድሪስ ያሉ ቦታዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

[addtoany]
የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሠማ ፣ ጀግናው ሠራዊታችን ሁመራንና ዋናውን መስመር ተከትሎ እስከ እንድሪስ ያሉ ቦታዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝ አረጋገጡ ።
በዚህ ግንባር በተደረገ ውጊያ ፣ ህብረተሰቡ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስበት ፣ ሠራዊታችን የነውጠኛው ታጣቂ ላይ ብቻ በማተኮር ሲቀነድበው ውሏል ።
ሜ/ጀ መሀመድ እንዳሉት ፣ በዚህ ውጊያ በርካታ ሰው ተማርኳል ፤ ቦታዎችና ንብረቶችም በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፣ ሠራዊታችን በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ የትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጠው ይገኛል ።
በሌሎች ግንባሮች ያለው ውጊያም ፣ በሠራዊታችን አጥቂነት ፣ በትህነግ ማፈግፈግ እንደቀጠለ ይገኛል ብለዋል ።
ሠራዊታችን የተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ፣ ጁንታው ምሽግ እንጂ ልማት ያልሰራባቸው በመሆኑ ፣ የረድዔት ድርጅቶች ከሚመለከተው የመንግስት አካል በመነጋገር ህዝቡን እንዲደግፉ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
ፅንፈኛው ፣ ጭፍሮቹን ፣ የኤርትራን ዩኒፎርም አስለብሶ ለፕሮፓጋንዳ የሚያሳየው የተለመደ ድራማ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፣ ልዩ ሀይል የሚላቸውን ሲቪል በማልበስ ባዶ እግራቸውን እንዲዋጉ በማድረግ ሲማረኩ ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲቪሎችን ወጋ በማለት ቅጥፈትን ስራው አድርጎታል ።
ለጁንታው የታጠቁ የትግራይ ልጆች ለሠራዊታችን እጃቸውን እንዲሰጡ ሜ/ጀ መሀመድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።