የሕወሓት ልዩ ሃይልና ሳምሪ በሚባል ያደራጀው ገዳይ ቡድን በማይካድራ ከተማ ባልታጠቁ ንፁሀን ላይ ጭፍጨፋ ፈፀመ

ጨካኙና አረመኔው የሕወሓት/ትህነግ ከማይካድራ ሲባረር በከተማዋና አካባቢው ባሉ ንፁሃን ላይ እጅግ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈፀሙን አማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። በማይካድራ ከተገደሉት ውስጥ አብዛኞቹ አማራዎች ቢሆኑም ከእነሱ ጋር ብዛት ያላቸው ኦሮሞዎችና ወላይታዎች ተገድለዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያት በሁመራ አከባቢ የሰሊጥ ምርት ለመሰብሰብ የሄዱ ናቸው።
ትህነግ እጅ ከፍንጅ የዘር ማጥፋት ሲፈፅም ዛሬ ተይዟል። መንግስት ሚዲያዎችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ይዞ የፈፀመውን ዘግናኝ ወንጀል ማጋለጥ አለበት። ይህ አረመኔ ቡድን በምንም ተአምር ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። እንዲያውም ዛሬ በንፁሃን ላይ የፈፀመው ወንጀል በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስከስሰው ነው።
የአይን ምስክር …. ከአብርሀጅራ እስከ ማይካድራ !!
By Dr Abrham Amare

ወገኖቻችን እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል ፤ ተረሽነዋል !! ማይካድራ እና አካባቢው ይኖሩ የነበሩ አማራዎች በሙሉ በሚባል ሁኔታ እዛው ነዋሪ በነበሩ ትግሬዎች ታድነዉ ተገድለዋል ። ሁሉም ጎረቤቱን ገድሏል ። ሚስት ባሏን ገድላለች ፤ በሚስቱ በገጀራ ተመቶ ሳይሞት የደረሰን ታካሚም አክመናል። በዚህ ደረጃ የአዉሬነት ተግባር በህዝባችን ተፈፅሟል!!
እኔ በህይወቴ በቀን ዉስጥ ከ200 በላይ ታካሚ ያዉም በድንገተኛ አደጋ ተጎድቶ በአንድ ቀን ዉስጥ ያዉም በአንድ ሆስፒታል ያየሁት ዛሬ ነዉ ። ለወደፊትም ማየቴን እርግጠኛ አይደለሁም ። ስራው እጅግ ቢያደክምም በቁጭት በእልህ የምንችለውን ሁሉ ስናደርግ ዉለናል!!
ለመከረኛዉ የአማራ ህዝብ ይህቺ ማድረግ የምንችላት ትንሽ ነገር ናት!!
~~~~
ህወሃትን እና ጀሌዎችን መረር ብሎ ከመደምሰስ ዉጭ ሌላ ምርጫ የለም ። ምንም ርህራሄ አያስፈልግም !!
በሌላውም የትግራይ አካባቢ የምትኖሩ አማሮች ተደራጅታችሁ ራሳችሁን ጠብቁ ፤ ራሳችሁን ከሞት ታደጉ!!
——————————————————
“አየሸሸ ያለው የትህነግ ልዩ ሃይልና ሳምሪ በሚባል ያደራጀው ገዳይ ቡድን በባልታጠቁ ንፁሃን ላይ ዘር የለየ ግድያ ፈጽሟል! ይህ ዓለም አቀፍ ወንጀል በትህነግ ሲፈፀም ባጅቷል።
አሁን በሌሎች ክልሎች በተላላኪዎቹ ሲፈጽም ቆይቶ በወልቃይት አማራዎች ላይም በድሞ በስውርና በተናጠል ሲያደርገው እንደነበረው ዛሬም በርካታ አማሮችን የኦሮሞ እና የወላይታ ብሄር ተወላጆችም ተገድለው ተመልክቻለሁ።
ይህ ቀን በሞያየ ካየኋቸውም በዘገባ ከደረሱኝም ቀናት ራሴን መቆጣጠር ያልቻልኩበት ነበር። ነገር ግን ጉዳዩን ለህዝብ ለማጋለጥ እና የአብመድ አደራየም ስለሚያስገድደኝ ተረጋግቼ ዘገባየን ፈጽሜያለሁ!!”
አሸባሪው ትህነግ በንፁሃን ላይ የፈፀመው እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በአማራ ቲቪ ተዘግቧል። በማሕበራዊ ሚዲያም የጅምላ ጭፍጨፋው ሰለባ ፎቶዎች እየወጡ ነው!
የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የመከላከያ ሰራዊቱ የትህነግን አሸባሪ ኃይል በማጣደፍ ላይ ነው። ይህ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ እጅግ የሚያምም ቢሆንም የትህነግ ኃይል መሬት ላይ እየተመታ መሆኑን አምነን በጥንቃቄ ማጋለጥ ይኖርብናል።
ይህ ቀሚስ ለብሶ እግሬ አውጭኝ እያለ ያለ ኃይል ትንፋሽ ለማግኘት ጉዳዩን የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲሆን እየጣረ ነው። ትህነግ እንደፈለገው ሳይሆን ጦርነቱ ከእሱ ጋር ብቻ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ አዋጩ መንገድ ነው። ትህነግ ጦርነት የገጠመው ከሕዝብ ጋር ነው ላልነው ግን ራሱ ዛሬ በርካቶችን በጅምላ ጨፍጭፎ አረጋግጦልናል።
ትህነግን የምንበቀለው እሱ በፈለገው መንገድ አይደለም። ትህነግን የምንበቀለው በጦር ሜዳ በማንበርከክ ነው። ትህነግን የምንበቀለው የገባበት ድረስ የታጠቀ ኀይሉን ድራሹን በማጥፋት ነው። ትህነግን የምንበቀለው የሽብር ቡድኑን ጠንሳሾች የገቡበት ገብቶ ለሕግ በማቅረብ ነው! ትህነግን የምንበቀለው ከእነ ምናምኑ በመንቀል ነው!