መንግስት የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ከማንም በላይ ሰፊውን ትግራዋይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው – ጠ/ሚ አብይ አህመድ

መንግስት የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ከማንም በላይ ሰፊውን ትግራዋይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
መንግስት በትግራይ የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ዓላማው ስግብግቡን የመቀሌ ጁንታ ለሕግ ተገዥ የማድረግና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን ማስጠበቅ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ይህ እርምጃ ከማንም በላይ ሰፊውን ትግራዋይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ወንድምና እህት ትግራዋይን ማንነታቸውን ያማከለ ለምንም አይነት ሕገወጥ ድርጊት ሰላባ እንዳይሆኑ የማድረግ ሀላፊነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ እንዳለብን ከአደራ ጭምር ጋር አሳስባለሁ ብለዋል።