ህወሓት የማንነት ጥያቄ ባነሳው የራያ ሕዝብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስድ ስጋት አሳድሯል

ህወሓት የማንነት ጥያቄ ባነሳው ህዝባችን ላይ የበቀል እርምጃ ሊወስድ ስለሚችል ስጋት እንዳለው የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ራዴፓ/ ገለጸ፡፡ VOA Amharic

የፌዴራሉ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ የጠየቀው ራዴፓ የመንግሥትን ወታደራዊ እርምጃ እንደሚደግፈው አረጋግጧል፡፡

የፌዴራሉ ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጥቃት ለመሰንዘር ህወሓት አጥፊዎችን ማሰማራቱን ገልጾ፣ ከነዚህ መሃል የተወሰኑትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡ ትግራይን ከአማራ ክልል በሚያገናኘው ድምበር አካባቢዎች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።