የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከነገ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ሣምንት የሚቆይ ጸሎትና ምህላ በሁሉም እምነት ተቋማት እንደየ እምነት ስራቱ እንዲከናወን ተገልጿል።
የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት ከሁሉም በፊት ቅድሚያ ለሀገር ሠላም እና መረጋጋት በመስጠት በመካከላቸው የተጀመረውን የእርስበርስ ግጭት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያቆሙ ተጠይቋል።