ኢትዮጵያ፡ የዩኒቨርሲቲዎች መከፈት እና የተማሪዎች ስጋት

በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት ለበርካታ ወራት ተቋርጦ የነበረው የዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት በቅርቡ ይጀመራል። ይህን ተከትሎ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ተስተውሎ የነበረው የጸጥታ ስጋት ከግምት በማስገባት የተማሪዎች ደህንነት ሁኔታ ስጋት ውስጥ የከተታቸው በርካቶች ናቸው። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ የዩኒቨርሲቲዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደ…