በቃሊቲ እስረኞች የዛሬ ጠዋት ቆጠራ ላይ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት በርካታ እስረኞች ተጎዱ ።

የቃሊቲ ተኩስ ጉዳይ

-አመፁ የተነሳው ማታ ከምሽቱ 2 ሰአት ዜና በኋላ ነው
ከምሽቱ 3 ሰአት ጀምሮ የማ/ቤቱ ሀላፊዎችና ፌደራል ፖሊሶች እስረኛውን በየተራ በማስወጣትና ከመካከላቸው የተወሰኑትን በመምረጥ ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል

-ወዳልታወቀ ቦታ ከተወሰዱት መካከልም አበበ ኡርጌሳ: ሌሊሳና ሌሎችም የሽብር እስረኞች ይገኙበታል

-ጠዋት አመፁ በድጋሚ የተቀሰቀሰውም ማታ የተወሰዱ ልጆች ይመለሱ የሚመለከተው አካልም ያናግረን በሚል ጥያቄ ነው

-ወደ ታራሚዎች በተተኮሰ ጥይት እስካሁን በታወቀ መረጃ
አብዱ አወል
ዳዊት ገብረ እግዚአብሄር
ዮናስ ነጋሲ በጥይት ቆስለዋል

-ታራሚው በሙሉ በጭስ ቦንብ ታፍኗል እስካሁን በጥይት የተመቱትን ጨምሮ ወደ ህክምና የተወሰደ የለም

~ትናንት ማታ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት ውጭ ክሳቸው እንደማይነሳ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሰጠውን መግለጫ የሰሙ እስረኞች “እኛስ ኢትዮጵያዊ አይደለንም?” ሲሉ ጩኸት አሰምተዋል

~ምሽት አካባቢ ፖሊሶች የእስረኞቹን ክፍሎች በማንኳኳት “መውጣት ከፈለጋችሁ አሁን ውጡ” እያሉ ሲዝቱ አምሽተዋል

~ዛሬ ጠዋት በቆጠራ ሰዓት እስረኞች ጩኸት ሲያሰሙ የፖሊስ መልስ ጥይት ሆኗል

~ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይትም እስረኞች እንደተጎዱ ለማወቅ ተችሏል