የእንጦጦ ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት ተካሄደ

“ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት አካል የሆነው የእንጦጦ ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት ተካሄደ።
ፓርኩ አገርኛ ስያሜዎችን እና መዝናኛ ዘርፎችን ባካተተ መንገድ የተገነባ ሲሆን፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።
የፓርኩ ምረቃ ከተከናወነ በኋላም ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል። በፓርኩ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በእንጦጦ ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:

• ለፓርኩ ግንባታ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
• ፓርኩን በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ለሰሩ ባለሙያዎች ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
• ይህ አገር ሊቀየር ይችላል፤ በተፈጥሮ የበለጸገች አገር ስለሆነች ከተባበርን
በየዓመቱ እንደዚህ ዓይነት ድንቅ ስፍራ መስራት እንችላለን፤ የሚያስፈልገው
ትብብር ነው፡፡
• አርት ወሳኝ ነው፤ የአርት ሙያ ያላቸው ግን ቦታ ያጡ ሰዎች አሉ እና በፓርኩ
የአርት
ጋለሪን የሰሩ አካላትና በፓርኩ ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን የሰሩ አካላትን
አመሰግናለሁ፡፡
• መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለገበታ ለሸገር ያደረገችሁትን አስተዋጽኦ ከዚህ በኋላም
በገበታ ለአገር እንዲትቀጥሉ እጠይቃለሁ፡፡
• ከእርዳታና ከልመና የምንወጣበትን ስራ መስራት አለብን፡፡
• ብዙ እንጦጦዎችን፣ ብዙ ሸገሮችን፣ ብዙ የሚያማምሩ ስራዎችን ለመስራት
እንተጋለን፡፡