ከመተሃራ አልጌ የሚባል ቦታ 40 አማራዎች በአከባቢው አመራሮች አነሳሽነት ተፈናቅለዋል።

ሌላ የአማራ መፈናቀል ዜና!

የካቲት 8/2010 ዓም ከመተሃራ አልጌ የሚባል ቦታ 40 ያህል አማሮች በአከባቢው አመራሮች አነሳሽነት ተፈናቅለዋል። በአሁኑ ወቅት 15 የፈናቃዮች ደጀን ከተማ ይገኛሉ። 17 አባውራዎች ወደወሎ ሄደዋል ተብሏል። ደጀን የሚገኙት:_

1) መለሰ ሀይሌ፣ ሁለት ልጆች፣ ባለቤቴ ጋር በኦህዴድ አመራሮች ተባርሯል። ባለቤቱ ባንቺአይሞሉ ምናለው እና ልጃቸው ተመስገን መለስ(የ8አመት)፣ ፍቅርተ መለሰ(3 አመት) ሲሆኑ ሁለቱም ልጆቻቸው ሕመም ላይ ናቸው።

2) ካሳ ወንድይራድ ከሁለት ልጆቿ ጋር ኦህዴድ አፈናቅሏታል። ታደሰ ይፈርድ(16 አመት) እንዲሁም ረድኤት ይፍረድ (9 አመት) ልጆች ናቸው።

3) ትብለጥ አድማሱ ከሁለት ልጆቿ ጋር ተፈናቅላለች። በረከት አምጤ (12 አመት)፣ በሱፉቃድ አምጤ (3 አመት) ልጆች ናቸው።

4) ተስፋዬ እጅጉ ከባለቤታቸው ደመቁ ጤናውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል። አቶ ተስፋዬ አንድ እጅ ጉዳይ ያለባቸው ሲሆን የ5 አመት እና የ6 ወር ልጆች አሏቸው።

5) እየሩስ ከ4 አመት ልጇ ጋር ተፈናቅላለች

6) አለሙ አበራ የሚባል ሰው በወቅቱ እንደተገደለና ብዙዎቹ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልፆአል።

አመራሮቹ “አማራን አስወጡት” ብለው አዝዘው እንዳፈናቀሏቸው ተፈናቃዮቹ በስልክ ገልፀውልኛል። ደጀን ከተማ የሚገኙትን 15 ተፈናቃዮችን ግለሰቦች ብቻ የተወሰነ ድጋፍ እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ በችግር ላይ እንደሚገኙም ተገልፆአል።