ፋና ቴሌቭዥን የአፋር ወጣቶችንና የአገር ሽማግሌዎችን አቤቱታ አፈነ ።

ፋና ቴሌቪዥን ድምፃችን አፈነ

ፋና ቲቪ ድምሮም ወያኔ ለኘሮፖጋንዳ የከፈተ channel መሆኑ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ዶክተር አብይ ከመጡ ቡሗላ የተወሰነ መሻሻሎችን አድርጎ ገልልተኛ የህዝብ ድምፃች የሚሰሙበት ህዝባዊ ወገንተኝነት ያለው የተለወጠ ሚዲያ መስሎን ነበር፡፡፡


እውነተው ግን ለካ ውሸቱን ነው የተመረጠ ወያኔ የሚያምንበት የፈቀደ ዜና ብቻ ነው የሚያቀርበው፡፡ ከሳምንት በፊት ከአፋር አምስት ዞን የተወጣጡ በክልሉ ህጋዊ የመብት ጥሰት የደረሰባቸው የአፋር ወጣቶችና የአገር ሽማጊሌዎች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በቁጥር ከ20 በላይ የሚሆኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ፋና ቴሌቪጅን ቅጥር ግቢ በማገኘት በአፋር ክልል በማህበረሰቡ ላይ እየደረሰ ያለው በደል ከየዞኑ የተመረጡ ሠዎች ቃላቸውን ለፋና ጋዜጠኞች የሠጡ ሲሆን የድርጅቱ ሙያተኞች አቤቱታ አቅራቢዎች የሠጡን ቃል ለማመሳከር የክልሉ አመራሮች አድራሻ ወደሰው በቅርብ ቀን እናስተላልፋለን ያሉት ዜና እነሆነ ከሳምንት በላይ ሳይታላለፍ ቀረ፡፡ ነገሩን ስናጣራ ግን የፋና ኘሮድካስት ሐላፊ ዜና እንዳይተላለፍ ትዕዛዝ መሠጠቱን ለመረጋገጥ ችለናል፡፡

ለካ አሁንም የፋና ወያኔ ከአፈና አልተላቀቀም፡፡ ድምፃቸው የታፈነው የአፋር ተወካዮች ህጋዊ መብታቸውን ለማስከበር በቅርብ ግዜ ወያኔ ከአብዴፓ ጋር በማበር ድምፃችንን ያፈነብን (የሚዲያ ነፃነታችንን የነፈገን) የፋና ቴሌቪጅን በመቃወም በአዲስ አበባ በቁጥር በርከት ባለ የቅሬታ አቅራቢዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ሚኒስተር ፊት የሠላማዊ ተቃውሞ ድምፅ የምናሰማ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ቀን ልክ እንደፋና ቅሬታችን ተቀብሎን ድምፃችንን ለኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ላቀረበልን ኢትዮጵያ ቴሌቪጅን የተሰማንን አክብሮትና ምስጋና ከወዲሁ እናቀርባቡን፡፡ ፋና የህዝብ ወገን አይደለም፡፡ ለ27 አመታት ስታፈኑ እንደነበሩ የቅሬታ ድምፆች ዛሬ የህወሓትና ደጋፊ ቡድኖች ትዕዛዝ በመቀበል የህዝብ ድምፆች እያፈነ ይገኛል፡፡ ለዚሁም ምስክሮች እኛ ተበዳይ የአፋር አቤቱታ አቅራቢዎች ምስክሮች ነን፡፡

ፋና ልክ እንደ ENN የህወሓት ልሳን በመሆኑ ሊዘጋ ይገባል፡፡ ድምፆችን ማፈሰን፡ ንግግሮችን መከልከል በወያኔ ዘመን ቀረ፡፡ አሁን ጊዜው ተቀይሯል ፋና የአብዴፓ አንዱ አካል መሆኑን በተጨባጭ አረጋግጠናል፡፡