አርበኛ ዘመነ ካሴ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው!

አርበኛ ዘመነ ካሴ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው!

ከ2004 ዓም ጀምሮ በኤርትራ ከግቦት 7 ጋር እስከተለያየበት ጊዜ ድረስ የቆየው ታጋይ ዘመነ ካሴ ወደ አገር ቤት ለመግባት መወሰኑን አስታውቋል።

ዘመነ ከኤርትራ ከወጣ ወራቶች ቢቆጠሩም ከጤናው ጋር በተያያዘ በአርምሞ ቆይቷል። አሁን ያለውን አንጻራዊ ነጻነት በመጠቀም አገር ቤት በመግባት ለመታገል መወሰኑን ተናግሯል። ዝርዝር የዘመነን ቃለ ምልልስ ወደ ማታ ይዘን እንቀርባለን።

ዘመነ የፊታችን ረቡእ ሐምሌ 18 ቀን 2010 ዓም 7.30 ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በርካታ የአማራ ወጣቶች አቀባበል ያደርጉላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።